ኢሰመኮ ደረጃ 1 እውቅና ተሠጠው

0
763

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከዓለም አቀፉ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት ጥምረት (GANHRI) የደረጃ 1 ዕውቅና እንደተሠጠው ለማወቅ ተችሏል።
ይህን አስመልክቶም ኮሚሽኑ፣ ‹‹ያገኘነው ዕውቅና ሥራችንን በገለልተኝነትና በታማኝነት እንድንሠራ የበለጠ ያተጋናል›› ሲል ገልጿል።
ኮሚሽኑ፣ የፓሪስ መርሆዎች እየተባሉ የሚታወቁትን መመዘኛዎችን ሙሉ በሙሉ ማሟላቱ በዓለም አቀፉ ጥምረት ለረዥም ጊዜ በተካኼደ ግምገማ በመረጋገጡ፣ የደረጃ 1 ዕውቅና እንደተሰጠውም የኮሚሽኑ ኃላፊ ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) መናገራቸው ተሰምቷል።
ኮሚሽኑ ያገኘው ዕውቅና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ስብሰባዎች ላይ፣ በተባበሩት መንግሥታት ልዩ ልዩ አካሎች ውስጥ ለመሳተፍ እንዲሁም ምክረ ሐሳብና ግኝቶቹን ለማቅረብ ዕድል እንደሚስጠውም ተመላክቷል፡፡
የዓለም አቀፉ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት ጥምረት፣ ኢሰመኮ በፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ የሰብዓዊ መብቶችን ለማስጠበቅ እና ለማስፋፋት እየተጫወተ ላለው ሚናም አድናቆቱን ገልጿል ነው የተባለው። ዓለም አቀፉ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት ጥምረት 118 ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት የሆኑ አባላት ኅብረት ሲሆን፣ ከፓሪስ ሥምምነቶች ጋር የተጣጣሙ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት መመስረትን እና መጠናከርን ያበረታታል።


ቅጽ 4 ቁጥር 162 ታኅሣሥ 25 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here