በጎንደር ከተማ 5 ሺሕ 241 ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የልማታዊ ‹‹ሴፍቲ ኔት›› ፕሮግራም መጀመሩ ተሠማ

0
643

በጎንደር ከተማ አስተዳደር 5 ሺሕ 241 የሕብረተሰብ ክፍሎችን በከተሞች ልማታዊ ሴፍቲ ኔት ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮግራም በይፋ ተጀምሯል ተባለ።
የጎንደር ከተማ ምክትል ከንቲባ ባዩ አቡሃይ እንደገለፁት፣ በውጭ ኃይሎች እየታገዘ የሚንቀሳቀሰው ሽብርተኛ የተባለው የህወሓት ቡድን ወረራ በፈጸመባቸው አካባቢዎች በሰው ልጆች ላይ የሕይወት ሕልፈትና የንብረት ውድመት ማጋጠሙ ተመላክቷል።
የወደመውን ሀብት መልሶ ለመገንባትም ኹላችንም ርብርብ ማድረግ ይኖርብናል ያሉት ምክትል ከንቲባው፣ በከተማዋ በኹለተኛው ዙር የከተሞች ሴፍቲኔት ፕሮግራም 5 ሺሕ 241 የከተማዋ ነዋሪዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተናግረዋል።
የአማራ ክልል የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት አስተባባሪ ሀሰን ውህያ በበኩላቸው፣ ከከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም የሚገኘው ገንዘብ ከድህነት ለመውጣት በር ይከፍታል እንጅ ራሱ ከድህነት አያወጣም ማለታቸው ተነግሯል።
የሴፍቲኔት ፕሮግራም የሰዎችን የሥራ ዕድል ያሳድጋል ያሉት ሀሰን፣ ፕሮግራሙ የከተማዋን ልማት ለማፋጠንና የነዋሪዎችን ሕይወት ለመቀየርም ፋይደው ከፍ ያለ መሆኑን ገልጸዋል ነው የተባለው።
ፕሮግራሙ፣ የአካባቢ ፅዳትና የአረንጓዴ ልማት ሥራዎችን፣ የመሠረተ ልማትና የተፋሰስ ሥራዎችን ለማከናወን እንደሚያግዝ መጠቆማቸውን ከከተማው ኮሚዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።


ቅጽ 4 ቁጥር 164 ታኅሣሥ 16 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here