ምንጭ፡- ሲፒጄ (2021)
ሲፒጄ (ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች ተሟጋች ድርጅት) ድረ ገጽ በ2021 ባወታው መረጃ መሰረት የጋዜጠኞች መታሰር ከአመት ወደ አመት እየጨመረ መምጣቱን አመላክቷል።
በመረጃው መሰረትም ከላይ ከተዘረዘሩት የዓለም አገራት መካከል 50 ጋዜጠኞች በእስር ላይ ይገኙበታል የተባለችው ቻይና የዓለማችን ትልቁ የጋዜጠኞች እስር ቤት በመባል መሰየሙ ተመላክቷል።
በታሰሩ ጋዜጠኞች ብዛት ከቻይና በመቀጠል በኹለተኛ ደረጃ የምትገኘው ምያንማር ስትሆን፤ በ2021 ዓመት ከየካቲት አንድ መፈንቅለ መንግስት ጀምሮ 26 ጋዜጠኞችን አስራለች።
ከእነዚህ ኹለት አገራት በመቀጠልም 25 ጋዜጠኞችን በማሰር ግብጽ ከዓለም አገራት ውስጥ ሦስተኛውን ደረጃ የያዘች ሲሆን ኢራን ደግሞ የአስረኛውን ደረጃ መያዟን ድረ ገጹ ጠቁሟል።
ቅጽ 4 ቁጥር 164 ታኅሣሥ 16 2014



