ዓባይ ባንክ በትግራይ የሚገኙ 16 የባንኩ ቅርንጫፎች ያሉበትን ኹኔታ አንደማያውቅ ገለጸ

0
1042

ባንኩ በበጀት ዓመቱ 1.15 ቢሊዮን ብር አትርፏል

ዓባይ ባንክ አክሲዮን ማኅበር በትግራይ ክልል ያሉት 16 ቅርንጫፎቹ ምን ኹኔታ ላይ አንዳሉ እንደማያውቅ አስታወቀ።
በተለይም ጦርነት በነበርባችው የአማራ እና አፋር ክልሎች በሚገኙ የባንኩ ቅርንጫፎች ላይ፣ ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰም ማወቅ አለመቻሉን የባንኩ ስትራቴጂክ ሥራ አስፍጻሚ ወንድይፍራው መኮንን ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።
አክለውም፣ በደረስው ጉዳት ዙሪያ በብሔራዊ ባንክ ጥናት እየተጠና መሆኑን ገልጸው በቀጣይም ጥናቱ ሲያልቅ እንደሚገለጽ ጠቁመዋል።

ባንኩ ሰኔ 30/2013 በተጠናቀቀው በጀት ዓመት፣ የተቀማጭ ገንዝብ መጠኑ 48 በመቶ በመጨመር፣ ማለትም 7.8 ቢሊዮን ብር በመሰብሰበ፣ ከ22 ቢሊዮን ብር በላይ መደረሱን ለማወቅ ተችሏል። ሆኖም የጊዜ ገደብ ተቀማጭ ብር 16 በመቶ ቅናሽ በማሳየት፣ 891 ሚሊዮን ብር ያህል ገንዘብ እንደተሰበሰበ ለማውቅ ትችሏል። “ባንኩ በተከተለው አቅጣጫ የጊዜ ገደብ ተቀማጭ ድርሻን ወድ ሦስት በመቶ ዝቅ አድርጓል” ሲሉ ወንድይፍራው ጠቁመዋል።

ባንኩ ለዓባይ ሳዲቅ (ከወለድ ነጻ) እና ለመደበኛ የባንኩ ድንበኞች 20.1 ቢሊዮን ብር ብድር ያቅረበ ሲሆን፣ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ72 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል። ባንኩ ካቀረበው ብድር ውሰጥ 538 ሚሊዮን ብር ከወለድ ነጻ ለሆኑ ተጠቃሚ ድንበኞቹ ያቀረበው እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

ባንኩ ለአገር ዉስጥ ንግድና አገልግሎት ያቀረበው ብድር መጠን 20 በመቶ ድርሻ የሚይዝ ሲሆን፣ ለኮንስትራክሽን ዘርፍ ያቀረበው ብድር 16 በመቶውን ይይዛል። የማምረቻና ሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች እያንዳንዳቸው የስምንት በመቶ ድርሻ ሲወስዱ፣ ለትራንስፖርትና ኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ የቀረበው ብድር መጠን ቀሪውን የስድሰት በመቶ ድርሻ ወስዷል።

ባንኩ በዓመት ውሰጥ 3᎐4 ቢሊዮን ብር ገቢ ያገኘ ሲሆን፣ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ63 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተገልጿል። ከዚህም ውሰጥ 72 በመቶ የሚሆነውን ገቢ የሸፈነው ከወለድ የተሰበሰበ ሲሆን፣ ከኮሚሸን 19 በመቶ እና ከድርሻ ሽግሽግ የተገኘው ደግሞ ዘጠኝ በመቶ የሚሆነውን ድርሻ በመያዝ ለባንኩ ገቢ አስተዋጾ ማድረጉ ተነግሯል።

ከወጪ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻውን የወሰደው፣ ማለትም 36 በመቶ የሚሆነው፣ ለተቀማጭ ገንዝብ የተከፈለ ነው። 31 በመቶ የሚሆነው ደግሞ ለአስተዳደራዊ እና ለደሞዝ የወጣ መሆኑ የታወቀ ሲሆን፣ ከግብር በፊት ባንኩ 1.15 ቢሊዮን ብር ማትረፉን ለማወቅ ተችሏል። ባንኩ በበጅት ዓመቱ ከ2᎐3 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ያደረገ ሲሆን፣ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ49 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

ከተመሰረተ 11 ዓመት የሞላው ባንኩ፣ ያስመዝግበው ትርፍ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር 80 በመቶ የላቀ መሆኑን የገለጹት ሥራ አስፈጻሚው፣ አጠቃላይ የሀብት መጠኑም 29᎐9 ቢሊዮን ብር መሆኑን ጠቁመዋል። ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር 9᎐8 ቢሊዮን ብር ዕድገት ማሳየቱን ለአዲስ ማለዳ ገለጸዋል።

አባይ ባንክ አጠቃላይ ካፒታሉ 4᎐2 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ የተከፈለ ካፒታሉ ካለፈው ዓመት 30 በመቶ ጭማሪ በማሳየት 2᎐8 ቢሊዮን ብር ደርሷል። ይህም የሆነው ባለ አክሲዮኖች 642 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ተጨማሪ ድርሻዎችን በመግዛታቸው መሆኑ ታውቋል።
የባንኩ ድንበኞችን ቁጥር 46 በመቶ የጨመረ ሲሆን፣ በተጠናቀቀው ዓመት ከ 376 ሺሕ በላይ አዲስ ድንበኞችን በማፍራት አጠቃላይ የደንበኞቹ ቁጥር ከ1᎐2 ሚሊዮን በላይ መሻገሩ ተነግሯል።
ባንኩ ስኔ 30/2013 በተጠናቀቀው በጄት ዓመት 28 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ፣ የቅርንጫፎቹን ብዛት፣ ከወለድ ነጻ አገልግሎት የሚሰጡትን ጨምሮ፣ 286 ማድረሱን ለማወቅ ተችሏል።


ቅጽ 4 ቁጥር 164 ታኅሣሥ 16 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here