በጥር ወር 150 ሚሊዮን ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ ተይዟል

Views: 187

የጉምሩክ ኮሚሽን በጥር ወር ከ152 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃ እና ሕገ ወጥ ገንዘብ መያዙን አሰታወቀ። ይህም ከገቢ 121 ሚሊዮን ብር ሲሆን፣ ከወጪ ደግሞ 31 ሚሊዮን ብር በአጠቃላይ 152 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ተገልጿል።
በቁጥጥር ስር የዋለው የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴው በመጠን ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 75 በመቶ ብልጫ እንዳለው ታውቋል።
ከተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል ኤሌክትሮኒክስ፣ አልባሳት፣ አደንዛዥ እፆች፣ የጦር መሣሪያዎች፣ ምግብ ነክ ሸቀጣ ሸቀጦችና ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ወደ አገር እንዳይገቡና እንዳይወጡ በሕግ ክልከላ የተደረገባቸው ዕቃዎች ይገኙበታል።
ኮሚሽኑ የገቢና ወጪ ንግድን ለማቀላጠፍ የአሰራርና የሕግ ማሻሻያዎች አድርጎ እየሠራ እንደሚገኝ ገልጾ፣ በቀጣይነትም መሻሻል ያለባቸውን አሰራሮች በማሻሻል የበለጠ ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
ኮሚሽኑ ሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የኮንትሮባንድና ሌሎች የንግድ ማጭበርበር ወንጀሎች በሕጋዊ የንግድ እንቅስቃሴ፣ በሕዝብ ደኅንነት፣ በመንግሥት ገቢና በሌሎች ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገቶች ላይ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽዕኖ ለመከላከል ጠንካራ የሕግ ማስከበር ስርአት ዘርግቶ መሥራቱን እንደሚቀጥል አስታውቋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 67 የካቲት 7 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com