በጥር ወር ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በማስወገድ ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ ተገኝቷል

Views: 315

የአስራ አምስት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ንብረት የሆኑ 30 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በማስወገድ ከስምንት ሚሊዮን ብር በላይ መገኘቱን የመንግሥት ንብረት፣ ግዢ እና ማስወገድ አገልግሎት አስታወቀ።
ለሽያጭ ከቀረቡት 30 ተሽከርካሪዎች ንብረትነታቸው የ10 ፌዴራል ተቋማት የሆኑ 21 ተሸከርካሪዎች፣ ከመነሻ ዋጋ በላይ ላቀረቡባቸው 13 ተጫራቾች እንዲሁም ተወዳዳሪዎች ከፍተኛውን ዋጋ የሰጡባቸው 9 ተሽከርካሪዎችን ሽያጭ ጨምሮ በድምሩ 8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ተገኝቷል።
ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ጥር 2/2012 ጀምሮ ለተከታታይ 19 ቀናት ክፍት ሆኖ እንዲቆይ ተደርጓል የተባለ ሲሆን፣ ጥር 21/2012 ተከፍቷል።

ቅጽ 2 ቁጥር 67 የካቲት 7 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com