የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላሊባላ ከተማ በረራ ጀመረ

0
508

ሰኞ ታህሳስ 25/2014 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላሊበላ ዕለታዊ በረራውን ዛሬ ጀምሯል።

ወደ ከተማዋ በረራ የሚያደርገው የመጀመሪያ አውሮፕላን ዛሬ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ከ30 ላይ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ መነሳቱን ከአየር መንገዱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

አየር መንገዱ ወደ ከተማዋ መጓዝ የሚፈልጉ መንገደኞች በአየር መንገዱ መተግበሪያ በመጠቀም ቀጠሮ ማስያዝ እንደሚችሉ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላሊበላን ጨምሮ ከ20 በላይ የአገር ውስጥ መዳረሻዎች አሉት።

በኮቪድ-19 እና ህወሃት በከፈተው ጦርነት ምክንያት ከተጎዱ በቱሪዝም ዘርፍ ከሚተዳደሩ አካባቢዎች አንዱ የላሊበላ ከተማ ነው።

የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የሚዳሰስ ቅርስ ብሎ ከመዘገባቸው የኢትዮጵያ ቅርሶች አንዱ ነው።

የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከአለት ተፈልፍው የተሰሩ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ስልጣኔ ማሳያ ተደርገው ይቆጠራሉ።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here