ከባድ የእርሻና ኮንስትራክሽን መንጃ ፈቃድ አገልግሎት መሰጠት መጀመሩ ተገለጸ

0
817

ሰኞ ታህሳስ 25/2014 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ከባድ የእርሻና ኮንስትራክሽን መንጃ ፈቃድ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።

በአዲሱ የተቋማት አደረጃጀት መሰረት ቀደም ሲል በፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ሲሰራ የነበረው ከባድ የእርሻና ኮንስትራክሽን መንጃ ፈቃድ አገልግሎት ለአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ቢሮ በውክልና መሰጠቱ ይታወሳል፡፡

በዚህም መሰረት ቢሮው ከባድ የእርሻና ኮንስትራክሽን መንጃ ፈቃድ አገልግሎት መስጠት የጀመረ መሆኑ በመግለፅ ተገልጋዮች አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ገልጿል።

በመሆኑም አሽከርካሪዎች አዲስ መንጃ ፈቃድ ለማውጣት በሚሄዱበት ወቅት የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ወይም የታደሰ ፓስፖርት፣ ሲኦሲ ዋናውን፣ የ8ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ ዋናውን፣ እና የ10 ክፍል የትምህርት ማስረጃ ዋናውን ሆኖ ትክክለኛነቱ በአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የተረጋገጠ ሰነድ በመያዝ በአካል በመቅረብ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ ሲል ቢሮው አስታውቋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here