“የገና በዓል በሰላም እንዲከበር የፀጥታ አካላት ቅድመ ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ተግባር ገብተዋል”፦ ፖሊስ

0
1113

ሐሙስ ታህሳስ 28/2014 (አዲስ ማለዳ) የገና በዓል በሰላም እንዲከበር የፀጥታ አካላት ቅድመ ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ተግባር መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ታህሳስ 29 ቀን 2014 በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በከፍተኛ ድምቀት የሚከበረው የገና በዓል በሰላም እንዲከበር የፀጥታ አካላት የጋራ እቅድ አውጥተው ወደ ተግባር መግባታቸው፣ለቅድመ ወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ተግባር ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰሩ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ህዝብ በብዛት በሚንቀሳቀስባቸው በገበያ ስፍራዎችና በትራንስፖርት መጠበቂያ ቦታዎች የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከል የፖሊስ አባላት እንደተሰማሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ከዚህ ቀደም የተከበሩ ሀይማኖታዊና ብሄራዊ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ህብረተሰቡ ከፀጥታ ሃይሉ ጎን በመቆም የድርሻውን ማበርከቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውሶ የዘንድሮው የገና በዓል በሰላም እንዲከበር መላው የከተማዋ ነዋሪዎች የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት 991 ነፃ ስልክ ወይም

• አዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ 011-1-1-01-11
• አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-2-73-37-43
• አራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-1-57-34-26
• ኮልፌ ቀራኒዩ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-3-71-77-53
• ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-1-57-50-59
• ልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-5-15-37-60
• የካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-6-18-13-39
• ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-5-52-80-44
• ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-6-67-47-18
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-4-40-07-92
• አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-4-39-14-38
• ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-6-39-10-24 መስመሮችን መጠቀም የሚችል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በመጨረሻም ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስራው ስኬታማነት እያደረገ ላለው ቀና ትብብር የአዲስ አበባ ፖሊስ በመላው የፀጥታ አካለት ስም ምስጋናውን በማቅረብ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉ የሰላምና የደስታ እንዲሆንላቸው መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here