“የፈረንጆቹ 2021 ኢትዮጵያ በዲፕሎሚሲው ረገድ በክፋ የተፈተነችበት ሆኖ ያለፈ ነበር”፡-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

0
506
ሐሙስ ታህሳስ 28/2014 (አዲስ ማለዳ) ያሳለፍነው የፈረንጆቹ 2021 ኢትዮጵያ በዲፕሎሚሲው ረገድ በክፋ የተፈተነችበት ሆኖ ያለፈ ነበር ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በ2021 በርካታ ተግዳሮቶች በውጭ ግንኙነት መስክ ኢትዮጵያ ላይ ተደቅኖ እንደነበር የገለፁ ሲሆን፤ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታንና በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተካሄደውን ህግ የማስከበር ሂደት ኢትዮጵያን ለማጥቃት በጭንብልነት ተጠቅመውበታል ብለዋል።
ይህንንም በሰብአዊ መብት ሽፋን ጉዳዩን ወደተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና አውሮፖ ህብረት ወስደው ለማስጮህ መሞከራቸውን የጠቀሱት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ኢትዮጵያ ከወዳጅ አገራት ጋር ባደረገችው ጥረት የታለመዉ ጫና መክሸፋን ተናግረዋል።
ሚኒስቴሩ አክለውም በተለይም የኢትዮጰያን ድንበር ተሻግራ ከገባችው ሱዳን ጋር ችግሮቹ በሙሉ በጦርነት እንዲፈቱ ለማድረግ ከየአቅጣጫዎች ጫናዎች ሲሰነዘሩ ቢቆዩም ኢትዮጰያ ይሄንን አካሄድ ወደ ጎን በማለት ነገሮች ወደ ሰላም እንዲመጡ ስትሰራ የቆየችበት ዓመት ነበር ሲሉም ገልፀዋል።
በአንጻሩ ደግሞ ኢትዮጰያ ወዳጆቿን ጭምር በአንድ በማሰለፍ የበቃ ዘመቻ ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ በማድረግ ጫናዎቹን መመከት ችላለች ብለዋል።
አምባሳደር ዲና አክለውም አንዳንድ ምዕራባዊያንና የአውሮፓ አገሮች ዲፕሎማቶች ከኢትዮጵያ ሲሸሹ የ10 አገራት አምባሳደሮቹ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው የአገሪቱን ተደማጭነት ይበልጥ እንደሚያሳድገው ነው ብለዋል።
በቀጣዩ በ2022 የፈረንጆቹ የጊዜ ቀመርም በኢትዮጵያ ላይ ያልተገባ መረዳት ይዘው የሚገኙ አገራትን ወደ መረዳት እንዲመጡ በሚያደርጉ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባዩ አምባሳደር ዲና ተናግረዋል፡፡
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here