በሆሩ ጉዱሩ ወለጋ ዞን 433 የሸኔ አባላት ሲደመሰሱ 115ቱ መማረካቸው ተገለፀ

0
976

ማክሰኞ ጥር 3/2014 (አዲስ ማለዳ) በሆሩ ጉዱሩ ወለጋ ዞን እስካሁን በተካሄደ ኦፕሬሽን 433 የአሸባሪው ሸኔ ቡድን አባላት ሲደመሰሱ 115 አባላቱ ደግሞ መማረካቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ።

የዞኑን ሰላም ወደ ቦታው ለመመለስ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በቅንጅት በመስራት አስተማማኝና ውጤታማ ኦፕሬሽን በዞኑ እየተካሄደ መሆኑን የሆሩ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ በቀለ ደቻሳ አስረድተዋል። በዚህም ወደ 433 የሸኔ ቡድን አባላት ሲደመሰሱ 115ቱ ተማርከዋል፤ የቡድኑ የመረጃ እና የሎጅስቲክስ ክንፍ የሆኑ ወደ 623 የሚደርሱ አባላትን በቁጥጥር ሥር ማዋል ተችሏል ሲሉም ገልፀዋል።

እንዲሁም ጠላት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ዘመናዊና ኋላ ቀር የጦር መሳሪያዎችም ገቢ የተደረጉ ሲሆን የሽብር ቡድኑን እንቅስቃሴ በማጤን አስፈላጊውን ምላሽ እየሰጠን ነው ብለዋል። ሕዝቡን በማሳተፍና በማደራጀት ሰላምን የማረጋገጥ ሥራ በጋራ እየተሰራ ነው ያሉት አስተዳዳሪው በቀለ ደቻሳ አመራሩም ቡድኑ ከዞኑ ለማጥፋት በእቅድ እየተመራ አመርቂ ሚና እየተጫወተ ነው ሲሉም መግለፃቸውን ዋልታ ዘግቧል።

አሁን ላይ ቡድኑ በዞኑ የሚያካሂደው መስፋፋት ሙሉ በሙሉ እየደረቀ ሲሆን፤ በአጭር ጊዜም ዞናችንን ከአሸባሪው ሸኔ ነፃ በማድረግ ለሕዝባችን የተሟላ ሰላም እናረጋግጣለን ሲሉም በቀለ ተናግረዋል።

ተመሳሳይ ርዕሶች

በምዕራብ ኦሮሚያ ከ1 ሺህ 800 በላይ የሸኔ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ – ዜና ከምንጩ (addismaleda.com)

በምሥራቅ ወለጋ አንገር ጉትን ከተማ 400 ኩንታል እህል በኦነግ ሸኔ ተወርሷል ተባለ – ዜና ከምንጩ (addismaleda.com)

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ሐሮ ሊሙ ወረዳ 19 ሰዎች በኦነግ ሸኔ ተገደሉ – ዜና ከምንጩ (addismaleda.com)

በአርሲ ዞን ጥቅማጥቅም ለማግኘት የሸኔ አባል ነኝ ብሎ እጅ መስጠት የተለመደ ተግባር እየሆነ መምጣቱ ተነገረ – ዜና ከምንጩ (addismaleda.com)
____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here