ክንፈ “ግልፅነት የሌለው ክስ ቀርቦብኛል” አሉ

0
565

በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15ተኛ ወንጀል ችሎት የቀድሞው የ‘ሜቴክ’ ዋና ዳይሬክተር ክንፈ ዳኘው (ሜ/ጀነራል) በተከላካይ ጠበቃቸው በኩል ማክሰኞ፣ የካቲት 5 ባቀረቡት የክስ መቃወሚያ የፌደራል ዐቃቤ-ሕግ ባቀረበው ክስ የወንጀል ድረጊቱን እና ዝርዝር ሁኔታውን ከተገቢው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር የማይጣጣምና ግልፅነት የጎደለው መሆኑን ገልፅዋል።

“ካሊፎርኒያ ኢንተርናሽናል ኢንስቲዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ”ተብሎ ከሚጠራ ሐሰተኛ የፈጠራ ተቋም፤ ሐሰተኛ ኹለተኛ እና ሦስተኛ ዲግሪ እንዲሰጥ አድርገዋል በማለት የዐቃቤ ሕግ ክስ ቢያስረዳም። የትምህርት ተቋሙ ሐሰተኛ መሆኑን ዐቃቤ ሕግ የገለፀ ቢሆንም በሌላ በኩል በኮርፖሬሽኑ የትምህርትና ሥልጠና አፈፃፀም መምሪያ መሠረት ትምህርቱን የተማሩ ተማሪዎች የውል ገዴታ አለመፈረማቸውና ከኮርፖሬሽኑ የሰው ሀብትና ሥልጣን ማንዋል ቁጥር 9 ከሚፈቅደው ውጪ በኮርፖሬሽኑ ሠራተኛ ያልሆኑ ግለሰቦች በተቁዋሙ መማራቸውን ቢገለፅም ከመመሪያው አንፃር በቀጥታ ተከሣሽ የትኛውን መመሪያ እንደጣሰና ማን እንደጣሰው ካለመግለፁም በተጨማሪም ከመመሪያው አንፃር የትምህርት ተቁዋሙን ሀሰተኛ ሊያስብል የሚችለውን መነሻ መመሪያውን ጠቅሶ ከተከሳሽ የወንጀል ተሣትፎ አንፃር ተለያይቶና ግልፅ ሆኖ መቅረብ እንዳለበት በክስ መቃወሚቸው አቅርበዋል።

ከሳሽ የሚያቀርበው ክስ ተከሳሹ የተከሰሰበትን ወንጀል አይቶና ለይቶ መልስ ለመስጠትና መከላከል እንዲችል የወንጀሉን ዝርዝር ሁኔታ ከተገቢ የሕግ ድንጋጌዎች አንፃር ሊያቀርብ እንደሚገባው የተከሳሽ ጠበቃ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል።

የፌደራል ዐቃቤ ሕግ ተከሳሽ አድርጎቸዋል ብሎ የገለፃቸው ድርጊቶች “አስቀድሞ በመገናኘትና በመወሰን፤ በመመሳጠር፤ ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ በመከፋፈል፤ ጥቅሙን በእጅ ዙር የተካፈሉ መሆናቸውን”የገለፀ ቢሆንም መቼ የት ቦታ ምን ተብሎ እንደተወሰነ፤ በእጅ አዙር ተብሎ የተጠቀሰው የትኛውን ድርጊት ለመግለፅ እንደተፈለገና ተገኘ የተባለው ጥቅም ምን ዓይነት እና መጠኑ ካለመገለፁም በተጨማሪም አለአግባብ ተገልግለዋል የተባለውን ሥልጣን በትክክል የትኛው እንደሆነ ተለይቶ እንዳልቀረበ በክሱ መቃወሚያው ላይ ተገልጿል። በተጨማሪም “በሥልጣን ያለአግባብ መገልገል ወንጀል የሚሆነው የተከሳሹ ኃላፊነት በቀጥታ የሚያያዘው ከተጠያቂነት ጋር ሲሆን፤ የተጠያቂነት ወሰን እስከ ምን እና በምን አግባብ ወይም መነሻ የሚለውን ድንበር ለማበጀት መስፈርቱ የሥልጣኑ ምንጭ የሆንው ሕግ፤ የሥራ ቅጥር ውል፤ የሥራው ዝርዝር፤ የሥነ ምግባር ደንብ፤ ወይም ከኮርፖሬሽኑ የበላይ አመራር ቦርድ የተሰጠ ሥልጣን ሲኖርናይኸው ሥልጣን የተጣሰ ሲሆን ብቻ እንደሆነ”በክሱ መቃወሚያ ላይ ተካቷል። ፍርድ ቤቱ ዐቃቤ ሕግ የተከሳሽ መቃወሚያ ላይ።

ቅጽ 1 ቁጥር 14 የካቲት 9 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here