አርብ ጥር 6 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በአማራ ክልል በሽብርተኝነት የተፈረጀው የትሕነግ ኃይል ያደረሰውን ሰብኣዊና ቁሳዊ ውድመት የሚያሳይ የተጣራ መረጃ የመሰብሰብ ሥራ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ገለፁ።
በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች መረጃዎችን የመሰብሰብ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው እየሰሩ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የተጣራ እና ጥቅል መረጃዎችን በአግባቡ ሰንዶ መያዝ ያስፈልጋል ብለዋል።
መረጃው በተገቢው መልኩ ከተሰበሰበ በኋላም የትሕነግ ቡድን ያደረሰው ጥፋት እና ወንጀል ተጠቃሎ እንዲታተም ይደረጋል ብለዋል።
በሌላ በኩል በቡድኑ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎችን ወደ አካባቢያቸው የመመለስ ሥራም በተሳካ ሁኔታ እየተሰራ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ መገለጻቸውን ዋልታ ዘግቧል።
በአሁኑ ወቅት በተለያዩ አካባቢዎች የነበሩ መጠለያ ጣቢያዎች ተዘግተው ተፈናቃዮችን በአካባቢያቸው የማቋቋም ሥራ እየተሰራ ነው ብለዋል።
____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA



