ሱዳን የጋዝ ምርቶች በጋላባት በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ፈቀደች

0
1165

አርብ ጥር 6 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ተሽከርካሪዎች የጋዝ ምርቶችን በጋላባት በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንዲያስገቡ መፍቀዷን ካርቱም አስታውቃለች።

የሱዳን ጦር አዛዥ ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ጋዝ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ መፍቀዳቸውን የአገሪቱ ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል፡፡

እንደዘገባዎቹ ከሆነ ካርቱም ተሽከርካሪዎች ከኢትዮጵያ በምትዋሰንበት በገላባት በኩል እንዲገቡና ጭነው እንዲወጡ መፍቀዷን እየገለፁ ይገኛሉ፡፡

የሱዳን መንግስት ንብረት የሆነው ናይል ፔትሮሊየም የጋዝ ምርቶችን ወደ ኢትዮጵያ እንዲያስገባ እንደተፈቀደለትም ታውቋል፡፡

የናይል ፔትሮሊየም በአዲስ አበባ የሚገኘው የድርጅቱም፤ የጋዝ ምርቶችን በጋላባት በኩል ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት እንደተፈቀደለት አስታውቋል ሲል አል ዐይን ዘግቧል፡፡

ናይል ፔትሮሊየም ምርቶቹን ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት ለመኖሪያ ቤቶች እና ለንግድ ተቋማት በወኪሎች በኩል እንደሚያከፋፍል ተገልጿል፡፡
____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here