የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምርጫው እንዲራዘም ጠየቀ

Views: 481

የኢትዮጽያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምርጫ 2012ትን በተመለከተ በሰጠዉ መግለጫ ምርጫዉ እንዲራዘም መወሰኑን አስታወቀ።
ምክር ቤቱ “ከምርጫ የአገር ህልዉና ይቅደም” በሚል ርዕስ አርብ የካቲት 13/2012 በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ባደረጉት ዉይይት ምርጫዉ መራዘም አለበት ሲሉ በአብላጫ ድምፅ መወሰናቸዉን አስታውቋል።

ምክር ቤቱ የካቲት 7/2012 75 የፖለቲካ ፓርቲዎች በተገኙበት ባደረገው ውይይት ከአገር ህልዉና የምርጫ ሊቀድም ስለማይገባ፣ ፓርቲዎቹ ምርጫዉ ይራዘም የሚል ሐሳብ ማንፀባረቃቸውን ገልጿል።

ቀጣዩ ምርጫ ቦርድ ባወጣዉ የጊዜ ሰሌዳ ያካሄድ ወይስ ይራዘም በሚለዉ ጉዳይ ላይ የምክር ቤቱ አባላት አገራዊ ሁኔታዉን በማመዛዘን እና ጠንካራ የፖለቲካ ፓርቲ አለ ወይስ የለም በሚሉት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዉን እንደወሰነ አስታውቋል።

ምክር ቤቱ ምርጫ ቢራዘም ከሚመጣዉ ችግር ይልቅ ምርጫዉ በመካሄዱ የሚመጣዉ ችግር እንደሚብስ ስጋቱን ገልጿል። በአገሪቱ ያለዉ የሰላም እጦት ምርጫዉን ለማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ እንዳይኖር እንደሚያደርገውም አመላክቷል።

ለምርጫ መራዘሙም የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ምርጫ ቦርድ ተናበው የድርሻቸዉን መሥራት እንደሚኖርባቸዉ ያሳሰበው የጋራ ምክር ቤቱ፣ መንግሥት የፖለቲካ ፓርቲ እንቅስቃሴዎችን ነፃነት ከመገደብ መቆጠብ እንዳለበትም አስገንዝቧል።

ቅጽ 2 ቁጥር 68 የካቲት 14 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com