የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ዳያስፖራው በትራንስፖርት ዘርፍ እንዲሳተፍ ጥሪ አቀረበ

0
560

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንሰፖርት ቢሮ ኢትዮጵያውያን፣ ትዉልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያውያን ወዳጆች በመዲናዋ የትራንስፖርት የኢንቨስትመንት አማራጮች ተሳትፎ እንዲያደርጉ ቢሮ ጥሪ ማቅረቡ ተዘግቧል።

ዳያስፖራው በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሳተፍ ጥሪ ማቅረቡን አስታውቋል የተባለው ቢሮው፣ አገራዊ ጥሪን ተከትሎ ዳያስፖራዎች በከተማዋ የትራንስፖርት ዘርፍ በስፋት መሳተፍ እንዲችሉ በቂ ዝግጅት ማድረጉ ተሰምቷል።

የትራንስፖርት ቢሮው ኃላፊ ዳዊት የሺጥላ ለኢትዮጵያውያን፣ ትዉልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያውያን ወዳጆች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስቀደም፣ ወደ አገር ቤት የመጡ ዳያስፖራዎች በመዲናዋ የትራንስፖርት ዘርፍ እንዲሠማሩ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች መዘጋጀታቸውን ማስረዳታቸው ተነግሯል።

በመሆኑም፣ የከተማዋን ምጣኔ ሃብት ለማነቃቃት በርካታ ዕውቀትና ልምድ ያካበቱ ዳያስፖራዎች በሙያዎቻቸው ተሳትፎ እንዲያደርጉም የቢሮ ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል ተብሏል።
በከተማዋ በትራንስፖርት ዘርፍ የኢንቨስትመንት አማራጮች መሰማራት ለሚፈልጉ ኹሉ ቢሮው አስፈላጊዉን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም ዳዊት ማረጋገጣቸውም ተዘገቧል።

ትራንስፖርት ቢሮው በመጨረሻም፣ በከተማዋ በትራንስፖርት ዘርፍ ተሳትፎ ማድረግ ለሚፈልጉ ዳያስፖራዎች የተሳትፎ ፍላጎት መነሻ ሐሳብ ወይም ረቂቅ ‹‹ፕሮፖዛል›› በአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት አፍሪካ ኅብረት ፊት ለፊት በሚገኘው ዮቴክ ሕንፃ ማስገባት እንደሚችሉ ጠቁሟል።


ቅጽ 4 ቁጥር 167 ጥር 7 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here