የሱማሌ እና ኦሮሚያ ክልሎች በ40 ዓመት ውስጥ የከፋ ነው የተባለ ድርቅ እንዳጋጠማቸው ተነገረ

0
290

በኢትዮጵያ የሱማሌ እና ኦሮሚያ ክልሎች በ40 ዓመታት ውስጥ የከፋ ነው የተባለ ድርቅ እንዳጋጠማቸው የአሜሪካ መንግሥት ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት ዩ.ኤስ.ኤይድ ገለጸ፡፡
የክልሎቹ ነዋሪዎች ከብቶቻቸው ምግብና ውኃ በማጣታቸው እየረገፉ መሆናቸውንና ድርቁ የማኅበረሰቡ የኑሮ መሠረት የሆኑትን እንስሳቱን እየነጠቀ መሆኑም ተገልጿል።
የዓለም አቀፉ ነፍስ አድን ኮሚቴም በደቡበ ምሥራቅ ኢትዮጵያና በሱማሊያ በአርባ ዓመት ውስጥ ከታዩት የከፋ ድርቅ እንዳጋጠማቸውና በእነዚህ አካካቢዎች ለሰብዓዊ ቀውስ መባባስ ምክንያት መሆኑንም በቅርብ ጊዜ ባደረገው ግምገማ መመልከቱንም በሪፖርቱ አስታውቋል።
በሱማሌና በኦሮሚያ ክልሎች ለሦስተኛ ጊዜ የሚጠበቀው ዝናብ ባለመገኘቱ ባጋጠመው ድርቅ በአካባቢው የሚኖሩ የአርብቶ አደር፣ እንዲሁም የአርሶ አደር ማኅበረሰቦች ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰም እንደሆነ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ‹ኦቻ› ታኅሣሥ ወር ላይ ያወጣው ሪፖርት አመልክቷል።


ቅጽ 4 ቁጥር 168 ጥር 14 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here