ሐሙስ የካቲት 3 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በ35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ የተገኙት የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አኪንዉሚ አዴሲና በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ መደሰታቸውን ገለፁ።
ፕሬዝዳንቱ በቲውተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፣ “በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ወቅት ውድ ወንድሜን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አሊ በማግኘቴ በጣም ደስ ብሎኛል።“ ብለዋል።
አክለውም “ፈጣሪ የኢትዮጵያን ሰላም፣ እርቅ፣ አንድነት፣ መረጋጋትና ብልጽግናን አብዝቶ ይባርክ።“ ሲሉም መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n





