ሐሙስ የካቲት 3 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) 3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ የካቲት 3 ቀን 2014 ያካሄዳል፡፡
ጉባኤውን አስመልክተው ትናንት መግለጫ የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የፕሬስና ህዝብ ግኝኙነት ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር አዲስአለም እንቻለው፣ ምክር ቤቱ በ5 አጀንዳዎች ላይ እንደሚመክር ገልጸዋል፡፡
ምክር ቤቱ የ3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት የምስረታ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ላይ ተወያይቶ ማፅደቅ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2014 የመጀመሪያ ስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት የ2014 የመጀመሪያ ስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ማስለቀቅና ካሳ ጉዳዮች አቤቱታ ሰሚ ጉባኤን ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ማፅደቅ እና ልዩ ልዩ ሹመቶች ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ በጉባኤው የሚያከናውናቸው ተግባራት መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
የምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤ ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ እንደሚጀመር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት ኘረስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n




