10ቱ የአለማችን ሴት ሃብታሞች

Views: 558

ፋይናንስ ኦንላይን በቢዝነስ ትንታኔ ባወጣው ዘገባ፣ ዓለም ላይ ያሉ ቢሊየነር ሴቶችን ዝርዝር አስቀምጧል።
በዚህም መሠረት በደረጃ ከተቀመጡት ሴት ቢሊየነሮች መካከል አንደኛ ደረጃን የያዙት እንስት ፍራንኮይዝ ቢታንኮርት ናቸው። እኚህ ፈረንሳያዊት 53.2 ቢሊዮን ዶላር በሚደርስ የሀብት መጠን ነው ቀዳሚነቱን የያዙት።

ከእኚህ ቢሊዮነር በመቀጠል አሜሪካውያኑ አላይስ ዋልቶን እና ጃኩላይን ማርስ በተከታታይ ኹለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። አምስተኛ እና ሰባተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ቢሊየነሮችም አሜሪካውያን ሲሆኑ፣ በአራተኛ ላይ ያሉት ሴት ቢሊዮነር ቻይናዊት ናቸው።

ስድሰተኛዋን የዓለማችንን ሴት ቢሊዮነር መገኛ ጀርመን ስትሆን፣ ኔዘርላንድ፣ አውስትራያ እና ቺሊ ከስምንት እስከ ዐስር ድረስ ዝርዝሩ ላይ የተቀመጡ ባለሀብቶች መገኛ አገራት ናቸው።

ቅጽ 2 ቁጥር 70 የካቲት 28 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com