የቀድሞ የኦነግ ሊቀመንበር ገላሣ ዲልቦ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

0
747

ሐሙስ መጋቢት 22 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ለረጅም ጊዜያት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር የነበሩት ኦቦ ገላሣ ዲልቦ በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በገላሣ ዲልቦ እረፍት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በሀዘን መግለጫቸው “ኦሮሚያ ጠንካራ ሰው አጥታለች” ብለዋል።

“ገላሣ ዲልቦ የኦሮሞ ነፃነት ታጋይ ነበሩ” ያሉት ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ ሙሉ ህይወታቸውን ለኦሮሞ ሕዝብ የገበሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በሀዘን መግለጫቸው ለኦሮሞ ሕዝብ በሙሉ ብርታትን እመኛለሁ ብለዋል።

ኦቦ ገላሣ ዲልቦ የ1983 ሽግግር ወቅትን ጨምሮ ለረጅም ጊዜያት የኦነግ ሊቀመንበር ሆነው ማገልገላቸው ይታወሳል፡፡
________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here