ዳሰሳ ዘ ማለዳ የካቲት(16/2012)

Views: 109

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ሶማሊያዊያንን ለማቀራረብ የሚያደርጉት ጥረት እንቅፋት ገጠመው

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በሶማሊያው ፕሬዝዳናንትና እራሷን ነጻ አገር አድርጋ ካወጀችው ሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት መካከል መቀራረብን ለመፍጠር እያደረጉት ያለው ጥረት እንቅፋት እንደገጠመው ኢስት አፍሪካን የተባለው ጋዜጣ ዘገበ።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ጋር ሆነው የሶማሊላንድ ዋና ከተማ የሆነቸውን ሐርጌሳን ለመጎብኘት የነበራቸው ዕቅድ ተቃውሞ ገጥሞታል።በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የቀረበው የጉብኝት ሃሳብ በሶማሊያና በሶማሌላንድ አስተዳዳሪዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል ዓላማ ያደረገ ነበር። (ቢቢሲ አማርኛ)

 

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

የኢትዮጵ ምርጫ ቦርድ እስከአሁን ሰነዶቻቸውን ያስገቡ ፓርቲዎች ቁጥር ዝቅተኛ መሆናቸውን በመልገለጽ፣ ፓርቲዎቹ እንዲያሟሉት በዝርዝር የተገለፀላቸውን ሁኔታዎች በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ አሟልተው እንዲያቀርቡ ቦርዱ አሳሰበ። ምርጫ ቦርድ፣ ደብዳቤ እና ሟሟላት የሚጠበቅባቸው ዝርዝር ሁኔታዎችን የሚያስረዱ ሰነዶች የደረሳቸው የፓለቲካ ፓርቲዊች በሙሉ በደብዳቤ እስከ መጋቢት 03/2012 ከመድረሱ በፊት ሟሟላት የሚገባቸውን በሙሉ አሟልተው የምዝገባውን ስርዓት እንድትጀምሩ ሲል አሳስቧል። (ምርጫ ማለዳ)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

በምስራቅ ወለጋ በኩፍኝ በሽታ አምስት ሰዎች ሲሞቱ ከ700 በላይ ሰዎች ደግሞ በበሽታው መያዛቸው ተገለጸ። የዓለም አቀፋ የስደተኞች ድርጅት አይ ኦ ኤም እንዳለዉ በአሁኑ ወቅት በሽታዉን ለመከላከል ጠንካራ ስራ እየተሰራ መሆኑንና በበሽታዉ ምክንያት ሰዎች ህይወታቸዉን እንዳያጡ የሚደረገዉ ትግል መልካም ፍሬ እያፈራ መሆኑን ገልጿል፡፡በተለይም በሽታዉ በስፋት ታይቶባቸዋል የተባሉ አዳሬና ብሪንቃስ በተባሉ ቀበሌዎች ከ15 ሽህ በላይ በሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ማከናወኑን ድርጅቱ አስታዉቋል። (ኢትዮኤፍኤም)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

የአገር ውስጥ የምግብ ዘይት ፍጆታን ሙሉ በሙሉ መሸፈን የሚያስችለውና በኢትዮጵያዊ ባለ ሃብት በላይነህ ክንዴ፣ በቡሬ ከተማ እየተገነባ ያለው የዘይት ፋብሪካ ዛሬ የካቲት16/2012 በፌዴራልና በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ተጎብኝቷል። የፋብሪካው ሙሉ ግንባታ ከኹለት እስከ አራት ወራት ተጠናቆ ወደ ምርት ይገባል ተብሎም ይጠበቃል።(የኢትዮጵያ ፕሬሰ ድርጅት)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

ባለፉት ሰባት ወራት ለዓለም አቀፍ ገበያ ከቀረበ ቡና 407 ሚሊየን ዶላር መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ።በሰባት ወራቱ 150 ቶን ቡና ለዓለም አቀፉ ገበያ የተላከ ቢሆንም፥ የተገኘው ገቢ ከዛሬ 10 ዓመት በፊት ከነበረው ያነሰ መሆኑን የባለስልጣኑ ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ ገልፀዋል።በመጠን ከፍተኛ ቡና ለውጪ ገበያ ቢቀርብም የቡና ገበያ በመቀዛቀዙ ምክንያት የተገኘው ገቢ ዝቅተኛ መሆኑን አንስተዋል።(ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬተ)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

ብሔራዊ የውሃ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ሊሻሻል ነው። የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ብሔራዊ የውሃ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት ባካሄደበት ወቅት በተግባር ላይ የሚገኘው የውሃ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ በመሆኑ ወቅቱ ከሚጠይቀው የአሰራር ስርዓት ጋር የተጣጣመ፤ችግር ፈቺ የሆነ እንዲሁም የአገሪቱን ቀጣይ የእድገት አቅጣጫ ያማካለ ላመድግ እየተሸሻለ መሆኑ ተገልጿል። (የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር)
………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ያለ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ህጋዊ ለማድረግ የሚያስችል ምዝገባ በአቡዳቢ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ተጀምሯል። ምዝገባው ከየካቲት 12/ 2012 ወይም የካቲት 20/2020 (እ.አ.አ) እስከ መጋቢት 13/2012 ወይም እስከ መጋቢት 22 / 2020 (እ.አ.አ) ድረስ እንደሚቆይ ኤምባሲው ገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በመካከለኛው ምስራቅ አገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በተወያዩበት ወቅት የዜጎችን መብት ለማስከበር ጥያቄዎችን ለበተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት አቅርበው ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወሳል።(ኢዜአ)

 

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

መቀመጫውን ካሊፎርኒያ ያደረገው ጂ. ኤን. ቢ. የተሰኘ የቴክኖሎጂ ድርጅት በኢትዮጵያ ምርታማነትን በሚያሳድጉ የቴክኖሎጂ ምርቶች ላይ የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው አስታወቀየኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ጀማል በከር ኢትዮጵያ ቴክሎጂን በመጠቀም የምታመርታቸው ምርቶች ጥራታቸውን የጠበቁና በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፉ እና በተለይ በግብርና ምርቶች ማቀነባበር ዘርፍ ቴክኖሎጂን የሚጠቀም የአሰራር ስርዓት እንዲዘረጋ የሚደረገውን ጥረት ድርጅቱ እንዲያግዝ ጠይቀዋል። (የኢኖቬሽን ሚኒስቴር)

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com