ዕሮብ ጥር 18 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከዱባዩ ሎጂስቲክስ አገልግሎት አቅራቢ “ዲፒ ወርልድ” ጋር የተጀመረዉን ትብብር ለማጠናከር ከሥምምነት ላይ መደረሱን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ አስታውቀዋል፡፡
ሚኒስትሯ ከ“ዲፒ ወርልድ” ሊቀ-መንበርና ሥራ አስፈጻሚ ሱልጣን አህመድ ቢን ሱላዬም ጋር በዱባይ ገንቢ ውይይት ማካሄዳቸውንም ገልፀዋል።
ዲፒ ወርልድ የበርበራ ኮሪደርን ለማልማት እና ለመጠቀም እስከ 1 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስት ለማድረግ የሚያስችለውን የመግባቢያ ሥምምነት ባለፈዉ ዓመት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር መፈራረሙ ይታወሳል።
ከዚህም ጋር በተያያዘ በቆይታቸዉ በሥምምነቱ ዉስጥ የተካተቱ ተግባራት አፈፃፀምን በጋራ የገመገሙ ሲሆን በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይም መግባባት ላይ መደረሱን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n





