“የሕወሃት ቡድንን ተባብሮ ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ካልተቻለ የኢትዮጵያ ስጋት መሆኑን ይቀጥላል”፦ የአማራ ክልል መንግስት

0
641

ዕሮብ ጥር 18 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀውን የሕወሃት ቡድን ተባብሮ ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ካልተቻለ የኢትዮጵያ ስጋት መሆኑን ይቀጥላል ሲል የአማራ ክልል መንግስት አስታወቀ፡፡

ቡድኑ አሁንም በአማራ ክልል የተለያዩ ሥፍራዎች ላይ በየቀኑ ጥቃቶችን እየሰነዘረ፣ ንፁሃንን እያሰቃየና እየገደለ መሆኑን የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ ገልፀዋል፡፡

ማይፀብሪ፣ አዳርቃይ፣ ቆቦ፣ ኮረም፣ አላማጣ በየቀኑ ጥቃት የሚሰነዝርባቸው እና ከጦርነት አርፈው የማያውቁ አካባቢዎች እንደሆኑ ተናግረው ቡድኑ በእነዚህ አካባቢዎች አሁንም ፍላጎት እንዳለው ያሳያል ብለዋል፡፡

በከፍተኛ ደረጃ ሀይል እያሰባሰበና ሊወጋ እየተዘጋጀ መሆኑን የሚያሳዩ እንቅስቃሴዎች እያደረገ እንደሆነም ነው የተናገሩት፡፡

ሕወሃት አሁንም ልክ እንደ በፊቱ በሀሰት ትርክቱ እያሳመነ እንዲሁም እያስገደደ የትግራይ ህዝብን እያሰለጠነ እና እያዘመተ ነው ብለዋል፡፡

አሁን ባለዉ ሁኔታም ወረራ ለመፈፀም የተለያዩ ሙከራዎችን ቢያደርግም እንዳልተሳካለት እና ለሌላ ጥቃት እየተዘጋጀ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

ይህ ኃይል እስካልከሰመ ድርስ አርፎ የሚተኛ አይደለም ያሉት ዳይሬክተሩ እሰካሁንም ሽንፈቱን አምኖ ያልተቀመጠ እና ከስህተቱ የማይታረም መሆኑን እያሳየ ነዉ ማለታቸውን አሐዱ ዘግቧል፡፡

በዚህም ሁሉም ተረባርቦ ቡድኑን ማጥፍት ካልተቻለ ቡድኑ ለኢትዮጵያ ስጋት እንደሆነ ይቀጥላል ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here