የፌደራል እና የክልል መንግስታት የህግ አስፈጻሚዎች የግንኙነት መድረክ እየተካሄደ ነው

0
1110

ሐሙስ ጥር 19 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የፌደራል እና የክልል መንግስታት የህግ አስፈጻሚዎች የግንኙነት መድረክ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

መድረኩ በአገራዊ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ እየመከረ ይገኛል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር (ዶ/ር) ዐቢይ አህመድና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ የሁሉም ክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ ሀላፊዎች በመድረኩ እየመከሩ እንደሚገኙ ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

የፌደራል እና የክልል መንግስታት የህግ አስፈጻሚዎች የግንኙነት መድረክ ከወር በፊት በሰመራ መካሄዱ ይታወሳል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here