ሐሙስ ጥር 18 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እና የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።
ተቋማቱ የዕውቀት፣ የክህሎትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ሰነድ ነው የተፈራረሙት።
ከዚህ ቀደም የተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች በጋራ ለመስራት ውይይት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳንዶካን ደበበ ይህ የመግባቢያ ሥምምነት ለተማሪዎች ኢንተርንሺፕ የሚመቻችበት፣ መምህራኖች የተለያዩ ጥናቶችን የሚሰሩበት ይሆናል ብለዋል።
ሥምምነቱ ኮርፖሬሽኑ የሚገጥመውን ችግሮች ለመፍታት ዩኒቨርሲቲውን የሚያማክርበትና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የሚያስቀምጥበት ይሆናል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል።
የዪኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በስልጠና፣ በማማከር እንዲሁም ዘርፈ ብዙ ጥናቶችን በማድረግ ብዙ ሥራዎችን ማከናወን ይችላል መባሉን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና በዚህ ሥምምነት ተማሪዎቻችንም ይሁኑ መምህራኖቻችን በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ በመሄድ ማገዝና ትምህርታቸውን በተግባር መደገፍ ይችላሉ ብለዋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n



