ሐሙስ ጥር 18 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ተቋርጠው የቆዩት የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሽያጭ ሆነ በስጦታ የማስተላለፍ ውልና ሌሎችም አገልግሎቶች ከሰኞ ጥር 23/ 2014 ጀምሮ ወደ አገልግሎት እንደሚመለሱ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አስታውቋል።
የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሽያጭም ሆነ በስጦታ የማስተላለፍ ውልን የማረጋገጥ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ አቋርጦ የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ከሰኞ ጥር 23 ቀን 2014 ጀምሮ የተቋረጡትን አገልግሎቶች መስጠት የሚጀምር መሆኑን አገልግሎቱ አስታውቋል፡፡
አገልግሎቱን ለማግኘት ከዚህ ቀደም በተለመደው አግባብ በተቋሙ አሰራር መሠረት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት እና የተቋሙን ድረ-ገጽ www.dars.gov.et በመጠቀም ተቋሙ ባዘጋጀው የኦንላይን አገልግሎት መጠየቂያ ፎርም በመሙላትና ሲስተሙ የሚሰጠውን የጉዳይ መከታተያ ቁጥር በመያዝ በተቋሙ በሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በመቅረብ አገልግሎቱን ማግኘት የሚቻል መሆኑን የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ገልጿል፡፡
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n