ሐሙስ ጥር 18 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በቀድሞ የብሔራዊ መረጃ ደህንነት ዋና ዳሬክተር በነ ጌታቸው አሰፋ መዝገብ በሰብኣዊ መብት ጥሰት ተከሰው የነበሩት የቀድሞ የብሔራዊ መረጃ ደህንነት 22 ሰራተኞች እያንዳንዳቸው የ30 ሺህ ብር ዋስ አስይዘው ከእስር እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጠ።
ዋስትና ከተፈቀደላቸው መካከል የብሔራዊ መረጃ ደህንኘት ም/ዳሬክተር የነበሩት ያሬድ ዘሪሁን እና የተቋሙ የፀረሽብር ወንጀሎች መምሪያ ሀላፊ ተስፋዬ ኡርጌ ይገኙበታል።
ፍርድ ቤቱ የዓቃቢህግ የዋስትና መቃወሚያን ነጥቦችን ውድቅ በማድረግ በአንድ ዳኛ የድምጽ ተቃውሞ በሁለት ዳኞች አብላጫ ድምጽ ተከሳሾቹ እንዲከላከሉ በተባለበት በተሻሻለው አንቀጽ 423 እና አንቀጽ 556 መሰረት 30 ሺህ ብር ዋስ አስይዘው ከሥር እንዲፈቱ ተፈቅዷል ስትል ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ዘግባለች።
ብይኑን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
የዛሬውን ችሎት የኦ.ፌ.ኮ ፓርቲ አመራር የሆኑት ፖለቲከኛው ደጀኔ ጣፋ መታደማቸውም ታውቋል።
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n



