“መንግስት በቦረና ዞን በተደጋጋሚ የሚከሰተውን የድርቅ ጉዳት በዘላቂነት መፍታት የሚያስችሉ ተግባራትን ያከናውናል “፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

0
620

ሐሙስ ጥር 26 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) መንግስት በቦረና ዞን በተደጋጋሚ የሚከሰተውን የድርቅ ጉዳት በዘላቂነት መፍታት የሚያስችሉ ተግባራትን እንደሚያከናውን ጠቅላይ ሚኒስትር (ዶ/ር) ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቦረና ዞን በመገኘት ድርቅ ያስከተለውን ጉዳት የጎበኙ ሲሆን፤ በዞኑ የሚገኘውን የቦረና ከብት ዝርያ ማራቢያ እና ማስፋፊያ ማዕከልንም ተመልክተዋል፡፡

በጉብኝቱም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ መንግስት በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች እያቀረበ ካለው የእለት ደራሽ ድጋፍ ባሻገር ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ያደርጋል፡፡

በቦረና ዞን እየተገነቡ ያሉ አነስተኛ ግድቦችን በአብነት ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በዚህም በዞኑ በተደጋጋሚ የሚከሰተው ድርቅ የሚያስከትለውን ጉዳት በዘላቂነት መፍታት ይቻላል ነው ያሉት፡፡

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው የክልሉ መንግስት በዞኑ እየተገነቡ ያሉ አነስተኛ ግድቦችን በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ አገልግሎት እንዲሰጡ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዞኑ የተከሰተው ድርቅ በእንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የተናገሩት ደግሞ የቦረና ዞን አስተዳዳሪ አቶ ጃርሶ ቦሩ ናቸው፡፡
መንግስት የእንስሳት መኖን ጨምሮ የተለያዩ የእለት ደራሽ ምግብ ድጋፍ እያደረገ ስለመሆኑም ተናግረዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዞኑ እያደረጉት ባለው ጉብኝት በያቤሎ ከተማ የተገነባውን ኢፋ ቦሩ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤትንም ተመልክተዋል፡፡
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n    

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here