በነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች አቅርቦትና ሥርጭት ላይ ተበታትነው ሲሠሩ የነበሩ ተቋማት ሊዋሃዱ ነው ተባለ

0
467

በነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች አቅርቦትና ሥርጭት፣ እንዲሁም ጥራትና ክትትል ላይ ተበታትነው ሲሠሩ የነበሩ ተቋማት ሊዋሃዱ መሆኑ ተሰምቷል።
ከውህደቱ በኋላ በበላይነት የሚቆጣጠራቸው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሲሆን፣ ተቋማቱ እንደገና ተዋቅረው በአንድ የሚመሩበት ደንብና መመሪያ ተዘጋጅቶላቸዋልም ነው የተባለው።
እንደ ዘገባው ከሆነ፣ በዐዋጅ ከተቋቋመ ኹለት ዓመት ያለፈው የነዳጅና ነዳጅ ውጤቶች አቅርቦትና ሥርጭት ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን፣ በማዕድን ሚኒስቴር ሥር የነበረው የፔትሮልየም ምርቶች ጥራት ተቆጣጣሪ ዳይሬክቶሬት እና የኢነርጂ ባለሥልጣን ናቸው ሥራቸውን እና ጥሪታቸውን የሚያዋህዱት።
ከውህደቱ በኋላ በአንድ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት ሥር የሚጠቃለሉት የነዳጅ ጉዳይ የሚመለከታቸው ተቋማት፣ ሥልጣንና ተግባራቸው ለሁለት ወር ያህል ሲለይላቸው እንደነበርም ተጠቁሟል።
የነዳጅ ጉዳዮችና ግብይት ላይ ቁጥጥር ያደረጋል ተብሎ ኃላፊነት ተሠጥቶት የነበረውና ገና በመደራጀት ላይ የከረመው ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት ሥራ ሳይጀምር ነው ወደ ዳግም መደራጀቱ የገባው መባሉም ተመላክቷል።
በሌላ በኩል፣ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር ሲሸጥበት በነበረው ተመን እስከ የካቲት 30 ድረስ እንደሚቀጥል የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ይፋ ማድረጉም ተዘግቧል።


ቅጽ 4 ቁጥር 170 ጥር 28 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here