በመዲናዋ ደኅንነቱ የተጠበቀ የብስክሌት ትራንስፖርት ማስተግበር የሚያስችል ዕቅድና ዲዛይን መሪ ሐሳብ ይፋ ሆነ

0
1022

በአዲስ አበባ ከተማ ደኅንነቱ የተጠበቀ የብስክሌት ትራንስፖርት ማስተግበር የሚያስችል የዕቅድና ዲዛይን መሪ ሐሳብ ይፋ መሆኑ ተሰማ።
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ አስተባባሪነት ‹‹በብሉምበርግ ኢኒሼቲቪ›› ድጋፍ፤ በWRI ቴክኒካል ዕገዛ የብስክሌት መሠረተ ልማት ዕቅድና ዲዛይን መሪ ሐሳብ/ጋይድላይን/ ተዘጋጅቶ ይፋ መደረጉ ተዘግቧል።
መሪ ሐሳቡ የብስክሌት ኔትወርክ በማሳደግ እርስበርስ እንዲተሳሰር በማድረግ፣ የብስክሌት መጋራት ሥርዓት እንዲኖር የማይተካ ሚና እንዳለው ተብራርቷልም ነው የተባለው።
በመሆኑም፣ የብስክሌት ማቆሚያ ቦታዎችና መሠረተ ልማቶች እንዲኖሩ ከማድረግ ባለፈ በቂ የብስክሌት መለማመጃ ቦታዎች እንዲኖሩ ዕገዛ ያደርጋል ተብሏል። መሪ ሐሳቡ የተለያዩ አገር በቀልና ከሌሎች ዓለም አገራት የተገኙ ልምዶችንና ዕውቀቶችን ለመተግበር እንደሚያስችል ነው የተገጸው።
በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ተወካይ ቀጄላ መኮንን (ኢ/ር)፣ የከተማዋ ነዋሪዎችን የትራንስፖርት ፍላጎት መሸከም የሚችል አማራጮችን ለማበራከት ቀልጣፋና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትራንስፖርት ለማስፋት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል ተብሏል።
የትራንስፖርት አገልግሎቱን ዕገዛ የሚያደርግ የሞተር አልባ ትራንስፖርት በመዲናዋ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል የተባሉት ቀጄላ፣ የዐስር ዓመት ስትራቴጂና የሦስት ዓመት ማስተግበሪያ ዕቅድም ተዘጋጅቶ ወደሥራ እንደተገባ መጠቆማቸው ተዘግቧል።


ቅጽ 4 ቁጥር 170 ጥር 28 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here