የአደራ መልስ

0
528

በባሕር ዳር ለኤርትራዊያን ቤተሰቦች ከ20 ዓመታት በላይ በአደራ እንዲቆይ ሆኖ የተመለሰው የመኖሪያ ቤት ጉዳይ ከሰሞኑ አነጋጋሪ ከሆኑ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ወሬ አንዱ ነው።

በ1991 ባሕር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ይሰሩ የነበሩት ትውልደ ኤርትራዊው አብርሐም ደስይበለኝ በወቅቱ የኢትዮጵያና ኤርትራ የፖለቲካ ግብግብ ከሥራና መኖሪያ ቦታቸው ተፈናቅለው ወደ ኤርትራ እንዲሰደዱ አስገድዷቸዋል።

ያኔ መኖሪያ ቤታቸውን ለአባቷ የሥራ ባልደረባ ተፈራ አባተ እና በወቅቱ ተከራይ ለነበሩት መዓዛ ሳሙኤል አደራ ሰጥተው ስለመሔዳቸውም በወቅቱ ከአባቷ ጋር ወደ ኤርትራ የሔደችው ሰናይት አብርሐም ታስታውሳለች።

ከኢትዮጵያ ከወጡ ኹለት ዐስርት ከተቆጠሩ በኋላ ኹለቱ አገራት ዳግም ወደ ቅርርብና እርቅ መምጣታቸውን ተከትሎም እነ ሰናይት ከሰሞኑ ወደ ባሕር ዳር አቅንተዋል።

ከ20 ዓመት በፊት በአደራ ሰጥተውት ወደነበረው ቤት ሲሔዱ የገጠማቸውም የሰሞኑ አስደሳች የማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች መነጋጋሪያ ሆኗል።
አደራውን የተቀበሉት ኢትዮጵያዊያን ቤቱን ከመጠበቅ ባሻገር ለዓመታት ከኪራይ የሚገኘውን ገንዘብ ለእነ ሰናይት እንዲደርስ ሲያደርጉ መኖራቸው ገልፀው ከሰሞኑ ደግሞ ሳይላክ የከረመን 20 ሺሕ የኪራይ ብር ጨምሮ ቤቱን ለአደራ ሰጭዎቹ አስረክበዋል።

የሰጡትን አደራ ሳይሸራረፍ ያገኙት እነ ሰናይትም የኢትዮጵያዊነትን የታማኝነት ልክ ስለማየታቸው ገልፀው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 14 የካቲት 9 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here