ማክሰኞ የካቲት 1 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የብልጽግና ፓርቲ የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች የአቅም ግንባታ መድረክ ሥልጠና ዛሬ ተጀምሯል፡፡
የአቅም ግንባታ መድረኩ ዓላማ አመራሩ ወቅቱ የሚጠይቀውን የአመራር ብቃትና አስተሳሰብ እንዲያጎለብትና የመረጠውን ህዝብ በትጋትና በቅንነት እንዲያገለግል ለማስቻል ነው ተብሏል።
መድረኩ ጥንካሬዎችንና መልካም አፈጻጸሞችን አጠናክሮ በማስቀጠል የታዩ ውስንነቶችን ደግም ነቅሶ በማረም ህዝቡ በሚጠብቀው ደረጃ ለማገልገል የሚያስችል የአመራር አቅም ለማጎልበት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተነግሯል።
ለሚቀጥሉት አራት ቀናት በሚካሄደው በዚህ የአቅም ግንባታ መድረክ ላይ ከ320 በላይ አመራሮች፣ ሚንስትሮችና ሚንስትር ዴኤታዎችን ጨምሮ የተለያዩ የፌደራል ተቋማት ሀላፊዎችና ምክትል ሀላፊዎች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n




