በበጀት ዓመቱ ሰባት ወራት ከወጪ ንግድ አንድ ነጥብ 57 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል

Views: 193

በበጀት ዓመቱ ሰባት ወራት ከወጪ ንግድ አንድ ነጥብ 57 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ገቢው ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው 1 ነጥብ 41 ቢሊዮን ዶላር ጋር ሲነፃፀር፣ በ161 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ ማሳየቱን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በሰባት ወራት ውስጥም 196 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ፣ የተመዘገበው 1 ነጥብ 57 ቢሊዮን ዶላር መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገልጿል። በበጀት ዓመቱ ሰባት ወራት ከተያዘላቸው ዕቅድ በላይ ያስመዘገቡት የወጪ ንግድ ምርቶች አበባ፣ አትክልት፣ ፍራፍሬ እና ጫት ናቸው።

እንዲሁም የዕቅዱን ከ50 በመቶ እስከ 90 በመቶ ክንውን ያስመዘገቡ የወጪ ንግድ ምርቶች ደግሞ ቡና፣ የቅባት እህሎች፣ ስጋ፣ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች እንዲሁም የጥራጥሬ ሰብሎች ናቸው።

በሌላ በኩል ከተያዘው ዕቅድ አንጻር በውጭ ምንዛሬ ገቢ ከ50 በመቶ በታች ዝቅተኛ ገቢ ያስመዘገቡ የወጪ ንግድ ምርቶች ቁም እንስሳት እና ወርቅ መሆናቸውን የንግድና ኢንዱስተሪ ሚኒስቴር የወጪ ንግድ አፈጻጸም ሪፖርት ያሳያል።

የተገኘው ገቢ ዕድገት ቢታይበትም፣ የሚፈለገውን ያህል አለመሆኑን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 71 መጋቢት 5 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com