ዳሰሳ ዘ ማለዳ (መጋቢት 08/2012)

Views: 113

ቻይና የሚገኙ ኢትየጵያውያን ተማሪዎች ኮሮናን ለመከላክ ድንጋጤ ሳይሆን ጥንቃቄ ነው ሲሉ ለኢትዮጵያውያን ምክር ለገሱ

ከአንድ ወር በፊት ጭንቅ ላይ የነበሩት እና  በቻይና የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ተማሪዎች አሁን ከጭንቅት ወጥተው ለኢትዮጵያዊያን ምክራቸውን መለገስ የጀመሩ ሲሆን ተማሪዎቹም ኮሮናን ለመከላከል ድንጋጤ ሳይሆን ጥንቃቄ ማድረግ ነዉ የሚበጀዉ ብለዋል።

ዕዉቀትን ፍለጋ ከአገራቸዉ እና ከቤተቦቻቸዉ ተለይተዉ በቻይና ዉሃን ግዛት ትምህርታቸዉን ሚከታተሉ ከ300 በላይ ኢትዮጵያዉያን የሚገኙ ሲሆን በግዛቲቱ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበር ሊቀመንበር ዛህራ አብዱል ሃዲ ያሳለፉትን ስትናገር ፤ከኮሮና ቫይረስ እንዴት እራስን መጠበቅ እንደሚቻል እኛ ጥሩ ምሳሌ ነን በማለት “ቫይረሱ የተነሳባት በዉሃን ግዛት ብንገኝም ጥንቃቄ በተሞላዉ መንገድ እራሳችን በመጠበቃችን ዛሬ ላይ ደርሰናል” ለዚህም ኢትዮጵያዉያን ከድንጋጤ ተላቀዉ መከላከሉ ላይ ትኩረት አድርጉ ስትል ጠይቃለች። (ለኢትዮ ኤፍ ኤም)

……………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ በሪሶ ከኮሮናቫይረስ ነፃ መሆናቸው ተገለጸ። ኃላፊው ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ቫይረሱ ከተገኘበት ጃፓናዊ ጋር የቅርብ ንክኪ አንደነበራቸው ከታወቀ በኋላ ላለፉት 12 ቀናት ራሳቸውን ለይተው ተቀምጠው የነበረ ሲሆን አሁን ግን በተደረገላቸው ምርመራ ነፃ መሆናቸውን ገለጹ።ጃፓናዊው ከዶክትር ቶላ ጋር በተገናኘበት በዚያን ጊዜ “ገና ከውጪ አገር መምጣቱ ስለነበር ምንም አይነት የበሽታው ምልክት አይታይበትም ነበር” ብለው ለቢቢሲ መናገራቸውም የሚታወስ ነው።(ቢቢሲ አማርኛ)

……………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥረው በለይቶ ማቆያ ከነበሩ 113 ሰዎች መካከል 74ቱ ነፃ መሆናቸውን ኢንስቲትዩቱ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ በሽታ (የኮቪድ-19) አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
በኢትዮጵያ የኮሮና ቨይረስ የተገኘባቸው አምስቱ ታማሚዎች በለይቶ ማቆያ የህክምና መስጫ ማዕከል የቅርብ የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን በአሁን ወቅት በጥሩ ጤንነት ላይ መሆናቸውን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለጸ።(የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስትትዩት)

……………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

ከትናንት በስቲያ በአየር ጠባይ ምክንያት ተቋርጠው የነበሩ የሀገር ውስጥ በረራዎች መጀመራቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገለጸ። አየር መንገዱ በረራዎቹ በመቋረጣቸው መንገደኞች መጉላላት አጋጥሟቸዋል ያለ ሲሆን  በአሁኑ ወቅት በረራዎቹን ያስተጓጎለው የአየር ንብረት በመስተካከሉ ተጨማሪ አውሮፕላኖችን በመመደብ መጉላላት ያጋጠማቸውን ደንበኞቹን ለማስተናገድ እንደሚሰራ አየር መንገዱ ተናግሯል። በዚህም ከትናንት ጀምሮ በረራዎቹን እንደቀጠለ አስታውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከትናንት በስቲያ ወደ መቐለ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ሁመራ፣ አክሱም፣ ሽሬና ላልይበላ ሊያደርግ የነበረውን በረራዎች በአስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክንያት መሰረዙ ይታወሳል።(ኢዜአ)

……………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቴክኒክ ድጋፍ ከሚያደርጉ የውጪ ዜጋ ባለሞያዎች አንዱ የሆነውና የኮሮና ቫይረስ መያዝ ምልክቶችን አሳቷል ተብሎ የተጠረተረው ግለሰብ ከኮሮና ቫይረስ ነጻ መሆኑን ተገለጸ።የግለሰቡ የምርመራ ውጤት ከኮሮና ቫይረስ ነጻ መሆኑን ተከትሎ ቦርዱ ወደተለመደው የስራ እንቅስቃሴ መመለሱን  አስታውቋል።ቦርዱ ኢትዮጵያ ኮቪድ 19 ድንገተኛ ምላሽ ቡድንን እና የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ምስጋናውን አቅርቧል።(ምርጫ ቦርድ)

……………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

በተለያዩ ምርቶች ላይ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል የተባሉ 188 የንግድ ተቋማት መታሸጋቸው ተገለጸ።የአዲስ አበባ የንግድ ቢሮ እንደተናገረው በግብርና ምርቶችና በጤና መጠበቂያ ቁሶች ላይ ያላግባብ ዋጋ ጨምረው የተገኙ የንግድ ተቋማትና ፋርማሲዎች ላይ እርምጃው ተወስዷል። ትናንት መጋቢት 0/2012 በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በተደረገ ቁጥጥር የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል የተባሉ የንግድ ተቋማት እንደታሸጉ የቢሮው ምክትል ሀላፊ የሆኑት አከበረኝ ወጋገን ገልጸዋል።

……………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

ሱዳናውያን ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን በገንዘብ እንደሚደግፉ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያስታወቀ ሲሆን ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ገቢ ለማሰባሰብ በቅርቡ በተቀረጸው መርሃ ግብር ሱዳናዊያን የገንዘብ ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉም ብሏል። ለህዳሴው ግድብ ግንባታ የሚሆን ገቢ ለማሰባሰብ በፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ይፋ ተደርጎ በተጀመረው መርሀ ግብር በአገር ውስጥና በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በተጨማሪ ሱዳናዊያንም የገንዘብ ድጋፍ እያደረጉ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።(የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር)

……………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

ነብዩ ስሑል ሚካኤል ከመጋቢት 01/2012 ጀምሮ የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ጽኀፈት ቤት ኃላፊ ሆነው መሾማቸው ተገለጸ። ፓርቲው ለሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ በጻፈው ደብዳቤ ነብዩ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በትጋት እንዲፈፅሙም አሳስቧል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከዚህ ቀደም ከትግራይ ብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ጋር መክራቸውም ይታወሳል።

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com