ከደቡብ ምዕራብ ክልል ከ39 ሺህ ቶን በላይ የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ቀረበ

0
438

ከ39 ሺህ ቶን በላይ የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ።
የግብርና ሚኒስቴርና የፌደራል ቡናና ሻይ ባለስልጣን በደቡብ ምዕራብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ተገኝተው የቡና እደሳ ስራን ተመልክተዋል።
የክልሉ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በአገሪቱ ቡና፣ ቅመማ ቅመምና ሻይ ለማምረት ከፍተኛ አቅም ያለው መሆኑን አመላክቷል።
ክልሉ 541 ሺህ 141 ሄክታር ቡና ማምረት የሚችል አቅም ያለው ሲሆን፣ እስከ አሁን 300 ሺህ ሄክታር ገደማ የሚሆነው በቡና የተሸፈነ መሆኑም ተመላክቷል።
በ2014 በጀት ዓመት 61 ሺህ 864 ቶን የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ፣ እስካሁን ከ39 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለገበያ መቅረብ መቻሉም ነው የተነገረው።
በዘንድሮው አመት ለማዕከላዊ ገበያ ከቀረበው ቡና 20 ሺህ ቶን የሚሆነው ከቤንች ሸኮ ዞን መሆኑም መረጃዎች ያመላክታሉ።


ቅጽ 4 ቁጥር 175 መጋቢት 3 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here