በአማራ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍ በየወሩ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ኩንታል የምግብ እህል ያስፈልጋል

0
453

በአማራ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍ በየወሩ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የምግብ እህል እንደሚያስፈልግ ተገለጸ።
በአሁኑ ወቅት በጦርነቱ ምክንያት የምግብና መድኃኒት እጥረት ያጋጠማቸው ዘጠኝ ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ዜጎች እና በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ኹለት ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ዜጎች እርዳታ ይጠብቃሉ ነው የተባለው።
የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ኮሚሽን እንዳሳወቀውም፣ በክልሉ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍ በየወሩ አንድ ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ኩንታል በላይ የምግብ እህል ያስፈልጋል ነው ያለው።
እስካሁንም ይህን ቁጥር መሠረት በማድረግ መንግሥት 70 በመቶ፣ ሌሎች መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ደግሞ ቀሪውን በመሸፈን ዜጎችን እየደገፉ መሆኑም ተመላክቷል።
ህወሓት ከዚህ ቀደም ወርሯቸው በነበሩ አካባቢዎች ከነበረው ማህበረሰብ ከዘጠኝ ነጥብ ሦስት ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ለከፋ የምግብና የመድኃኒት እጥረት ተዳርጎ እንደነበርም ኮሚሽኑ ገልጿል።


ቅጽ 4 ቁጥር 175 መጋቢት 3 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here