10ቱ ዋጋ ግሽበት የከፋባቸው አፍሪካ አገራት

0
639

ምንጭ፡-የአፍሪካ ንግድ ሪፖርት ፤ 2018

ባለፈው ወር መጀመሪያ ይፋ የሆነው የአፍሪካ ንግድ ሪፖርት እንደሚያመለክተው የአፍሪካ አገራት አማካይ የዋጋ ግሽበት የ7 ነጥብ 2 በመቶ በ2018 (እ.አ.አ.) እድገት አሳይቷል። ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ1 ነጥብ 6 በመቶ ጭማሪ ሲያሳይ፤ በምክንያትነት የተጠቀሱት በተለያዩ የአፍሪካ አገራት የተደረገው የውጭ ምንዛሬ ተመን ማስተካከያ እና የበጀት ጉድለት መጨመር ናቸው።

እንደ ግብፅ፣ ናይጄሪያ እና አንጎላ ያሉ አገራት ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ከተመዘገበባቸው አገራት መካከል ሲመደቡ ስዋዚላንድ፣ ማሊ እና ካሜሮን ዝቅተኛውን የዋጋ ግሽበት አስመዝገበዋል። ኢትዮጵያ በ2018 የፈረንጆች ዓመት በአምስት ዓመት ውስጥ ትልቁን የዋጋ ግሽበት አስመዝግባለች። በሰኔ 2018 የአገሪቱ የዋጋ ግሽበት 16 ነጥብ 8 ደርሶ ነበረ። ይሁን እንጂ ከዚያ በኋላ በነበሩት ወራት ከፍተኛ ቅናሽ በማሳየት ባለፈው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ ወደ 10 ነጥብ 4 በመቶ ወርዷል።

ቅጽ 1 ቁጥር 15 የካቲት 16 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here