በኦሮሚያ ክልል የከተማ ውስጥ የህዝብ ትራንስፖርት ታገደ

Views: 390

በኦሮሚያ ክልል የከተማ ውስጥ የህዝብ ትራንስፖርት መታገዱን የክልሉ መንግስት አስታወቀ።

በዚህ መሰረት ታክሲ፣ ባጃጅ፣ ሞተር ሳይክል እና ጋሪ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት እንዲያቆሙ ተወስኗል፡፡

ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርትም ሙሉ በሙሉ እንዲቀረጥ ነው የክልሉ መንግስት ውሳኔ ያሳለፈው።

በክልሉ ያሉ የወረዳ ትራንስፖርቶች የመጫን አቅማቸውን 50 በመቶ እንዲቀንሱ፥ የመንግስትም ሆነ ፓርቲ የትኛውም አይነት ስብሰባ እንዳይካሄድ የተወሰነ ሲሆን ስብሰባ የጠራም ሆነ የተሳተፈ ህጋዊ እርምጃ እንዲሚወሰድበት ተገልጿል።

ህብረተሰቡም በየአካባቢው እንዲቆይ ያሳሰበው የክልሉ መንግስት ከገጠር ወደ ከተማ ከሚደረጉ ጉዞዎች እንዲቆጠቡም ነው ያሳሰበው።

እንዲሁም በክልሉ ያሉ ህዝብ የሚበዛባቸው ገበያዎች ለጊዜው ታግደዋል።

የሀይማኖተት ተቋማትም በርካታ ቁጥር ላላቸው ምዕመናን አገልሎት እንዳይሰጡ የታገዱ ሲሆን የሀይማኖት አባቶችም የተቀመጠውን አቅጣጫ እንዲያስፈፅሙ ጥሪ ቀርቧል።

ጭፈራ ቤቶች፣ ጫት ቤቶች እና ሺሻ ቤቶች የቫይረሱን ተጋላጭነት ስለሚጨምሩ ሙለ በሙሉ እንዲዘጉ ተወስኗል ነው የተባለው።

በክልሉ በሚገኙ ትልልቅ ከተሞች መግቢያ እና መውጫ ላይ የሰውነት ሙቀት ልኬት እንደሚካሄድ እና ተጠርጣሪዎች ክትትል እንደሚደረግላቸው ተገልጿል።

ጡረታ ለወጡ የህክምና ባለሙያዎች እና የህክምና ትምህርት እየተማሩ ለሚገኙ ተማሪዎች ጥሪ ሊደረግ ስለሚችል ራሳቸውን እንዲያዘጋጁም የክልሉ መንግስት አሳስቧል።

በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ኮሌጆች፣ የወጣቶች ማዕከላት እና ትምህርት ቤቶችም ለማቆያነት እንዲያገለግሉ ዝግጁ እንዲሆኑ አቅጣጫ ተቀምጧል።

የመንግስት ተቋማት አገልግሎት መስጠት የሚቀጥሉ ቢሆንም በቅርብ አለቆች አማካኝነት ወሳኝ የስራ ሂደቶችን በማሳተፍ ሌሎች ፍቃድ እንዲወጡ ተወስኗል።

ቫይረሱን በተመለከተ ሀሰተኛ መረጃ በሚያሰራጩ አካላት ላይ መንግስት አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድም ነው የገለፀው።

በዚህ ወሳኝ ወቅት የመንግስት አቅም ውስን መሆኑ ታውቆ ህብረሰተቡ፣ ባለሀብቱ እና ሌሎችም አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ ቀርቧል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com