በዓመት 10 ሺሕ ተሸከርካሪዎችን የሚገጣጥም ፋብሪካ ተከፈተ

0
490

በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ በዓመት 10 ሺሕ የሃዩንዳይ ተሽከርካሪዎችን የመገጣጠም አቅም አለው የተባለለት የማራቶን ሞተርስ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ተመረቀ።

በውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ሐሙስ የካቲት 14 የተመረቀው የአዲስ አበባው የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካ 500 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገበት በምረቃው ወቅት ተገልጿል።

ሚንስትሩ ወርቅነህ ገበየሁ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያ የኦቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ እንዲስፋፋ መንግሥት በዘርፉ ለተሰማሩና ወደፊትም መሰማራት ለሚሹ ባለሀብቶች ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል መግባታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት አሳውቋል።

ማራቶን ሞተርስ በአትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ባለቤትነት ከደቡብ ኮሪያ ሃዩንዳይ ሞተር ጋር በመተባበር የተገነባ መሆኑን ያሳወቀው ጽሕፈት ቤቱ ስምንት ዓይነት የተሽከርካሪ ሞዴሎችን እንደሚገጣጥምም አክሏል።

ሥራው ሲጀመር ለ200 ሰዎች የሥራ እድል ይፈጥራል የተባለለት ፋብሪካው በቀጣይ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ ደግሞ አንድ ሺሕ ሰዎችን ቀጥሮ ማሠራት እንደሚችል ተስፋ ተጥሎበታል።

በፋብሪካው የሚገጣጠሙ ተሸከርካሪዎችን እስከ 30 በመቶ አካል በአገር ውስጥ አምርቶ ለማሟላት እቅድም ተይዟል ተብሏል።

ቅጽ 1 ቁጥር 15 የካቲት 16 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here