የፌዴራል ፖሊስ እያገባደደ ባለው አዲስ የአደረጃጀት ጥናት ከዚህ ቀደም ያልነበሩ ልዩ ኃይል እና በአየር የሚታገዝ ቅኝት አድራጊ ቡድኖችን እያቋቋመ መሆኑን አስታወቀ።
የፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል እንዳሸው ጣሰው ሐሙስ የካቲት 14 በሰጡት መግለጫ እየተሠራ ያለው አዲሱ አደረጃጀት መልካም የሚባል ሒደት ላይ እንደሚገኝ ገልፀው፣ የከተማ ልዩ የፌደራል ፖሊስ ኃይል እና በአየር የታገዘ ክትትል ለማድረግ የሚያስችል የአየር ኃይል እየተደራጀ መሆኑን ጠቁመዋል።
የኮሚሽኑ የመዋቅር ማስተካከያ የፌዴራል ፖሊስ ሠራዊት አሰፋፈር እና አደረጃጀትን ከልሷል ተብሏል። አሰፋፈሩም ሰሜን፣ ደቡብ፣ ምዕራብ እና ማዕከላዊ ክላስተር በሚል እንዲደራጅ የሚደረጉ መሆኑ ተሰምቷል።
የፌዴራል ፖሊስ፣ የክልል ፖሊስ፣ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻዎች በሚባል የሚከፋፈሉት የፀጥታ አባላት ምን አይነት መሣሪያ ሊይዙ እንደሚገባ የሚደነግገው አዋጅ ዝግጅት መቀጠሉም በመግለጫው ተነስቷል።
ቅጽ 1 ቁጥር 15 የካቲት 16 ቀን 2011