መንግስት ወደ ትግራይ ክልል የእርዳታ እህል የጫኑ 21 ከባድ የጭነት መኪናዎች መጓዝ መጀመራቸውን አስታወቀ

0
1834

ሐሙስ መጋቢት 22 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በዓለም ምግብ ድርጅት አማካኝነት 21 ከባድ የጭነት መኪናዎች የእርዳታ እህል በመጫን በአፋር ክልል በአብኣላ መንገድ የሰብአዊ እርዳታ በየብስ ትራንስፖርት ወደ ትግራይ ክልል ማጓጓዝ መጀመሩን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አሰታወቀ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ወደ ክልሉ የሰብአዊ እርዳታ መጓጓዙን አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ እንደሚከተው ቀርቧል፦

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ውስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ ሁሉንም አማራጮች በመጠቀም የሰብአዊ እርዳታን ለማቅረብ እንቅስቃሴ መጀመሩ የሚታወስ ነዉ፡፡

ዉሳኔዉ ከተወሰነበት ቀን ጀምሮ የመድኃኒት፣ የህክምና መሳሪያዎች፣ ገንዘብና አልሚ ምግቦችን ረጂ ድርጅቶች በቻሉት መጠን በአየር ትራንስፖርት በየዕለቱ መጓጓዝ መጀመራቸዉንም ማሳወቃችን ይታወሳል፡፡

በዛሬዉ ዕለት ደግሞ በዓለም ምግብ ድርጅት አማካይነት 21 ከባድ የጭነት መኪናዎች የእርዳታ እህል በመጫን በአፋር ክልል በአብኣላ መንገድ የሰብአዊ እርዳታ በየብስ ትራንስፖርት ወደ ትግራይ ክልል መጓጓዝ ተጀምሯል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የሰብአዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦቱን በተሟላ ሁኔታ ለማስኬድ ከተባበረና ባለድርሻ አካላት ጋር ለመስራት ዛሬም ቁርጠኛ መሆኑን በድጋሚ ያሳውቃል፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here