በጂዳ እና አካባቢዋ ባሉ እስር ቤቶች ያሉ ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገር ቤት የመመለስ ሥራ ዛሬ ይጀመራል

0
838

1 ሺህ 831 በሳኡዲ አረቢያ እስር ቤቶች የነበሩ ዜጎች ወደ አገራቸው እንደሚመለሱም ተገልጿል

አርብ መጋቢት 23 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ከጂዳ እና አካባቢ ባሉ እስር ቤቶች እና ማቆያ ማዕከላት ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገር ቤት የመመለስ ሥራ ዛሬ እንደሚመለሱ ተገለፀ።

በተጨማሪም 1 ሺህ 831 በሳኡዲ አረቢያ እስር ቤቶች እና ማቆያ ማዕከላት ውስጥ የነበሩ ዜጎች ዛሬ ኢትዮጵያ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

ከሳኡዲ አረቢያ ወደ አገር ቤት ለመመለስ ከታቀደው 102 ሺህ ዜጎች መካከል ከ80 ሺህ የማያንሱት የሚገኙት በጂዳ እና አካባቢ በሚገኙ እስር ቤቶች እና የማቆያ ማዕከላት ነው።

ዛሬ በሚደረጉ አራት በረራዎች ከጅዳ 1438 በሳኡዲ አረቢያ በእስር ቤቶች እና ማቆያ ማዕከላት ውስጥ የነበሩ ዜጎች ኢትዮጵያ ይገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ከትላንት በስቲያ በጀመረው በሳኡዲ አረቢያ እስር ቤቶች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ሥራ፤ በአንድ ቀን ከሪያድ 936 ኢትዮጵያዊን ማምጣት የተቻለ ሲሆን ዛሬ ማለዳም 393 ዜጎች ወደ አገራቸው መመለሳቸውም ታውቋል።
________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here