ነዋሪዎቹ ከሙዚየሙ ግንባታ ባሻገር ቅርስ ማሰባሰቡ ትኩረት ይሰጠው አሉ

0
441

በደቡብ ወሎ አምባሰል ወረዳ እየተገነባ ያለው የይስማ ንጉሥ ሙዚየም በጎ ቢሆንም ቦታውን የሚስታውሱ ቅርሶች መጥፋታቸው እንዳሳሰባቸው ነዋሪዎች ገለፁ።

በሚያዚያ 1881 በኢትዮጵያና ጣሊያን የተፈረመውንና ኋላም ወደ አድዋ ጦርነት የመራውን የውጫሌውን ስምምነት ለማስታወስ በስፍራው የሙዚየም ግንባታ የካቲት 2010 መጀመሩ ይታወሳል። ግንባታው አሁን ላይ 50 በመቶ ደረሷልም ተብሏል። በውሉ መሰረት ግንባታው በጥር 2012 እንደሚጠናቀቅም ይጠበቃል።

በሙዚየሙ ግንባታ ደስተኛ መሆናቸውንና በጉልበትም እያገዙ መሆኑን የገለጹት የአካባቢው ነዋሪዎች ግንባታው ቢፋጠንም ከይሥማ ንጉሥ የውጫሌ ውል መፈራረሚያ ስፍራ ባሻገር አብረው የሚታወሱ ቅርሶች በዝርፊያና በሌሎችም መንገዶች መጥፋቸውን ተናግረዋል።

ሙዚየሙ ሲጠናቀቅ ‹‹ቤት ታቅፈን እንዳንቀር ስጋት አለን›› ያሉት ነዋሪዎቹ መንግሥትና ቅርሶች በእጃቸው የሚገኙ ግለሰቦች ቅርሶችን በማሰባሰብ ሒደት እንዲተባበሩ ጠይቀዋል።

በአራት ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ሙዚየሙ በመንግሥት የ25 ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ብር በጀት እየተሰራ ነው።

ቅጽ 1 ቁጥር 16 የካቲት 23 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here