ሰባት ፓርቲዎች ግንባር ፈጠሩ

0
506

ሰባት ተፎካካሪ ፓርቲዎች ተጣምሮ፣ በግንባር አብሮ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የስምምነት ሰነድ፣ ረቡዕ የካቲት 20 ቀን 2011 ዓ.ም ተፈራረሙ፡፡

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ)፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ኅብረት (ኢድኅ)፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢብአፓ)፣ የአፋር ሕዝቦች ፍትሐዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የአፋር ሕዝብ ነጻነት ፓርቲ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ፍትሐዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የአገሪቱን ወቅታዊ ተጨባጭ ሁኔታ በመገንዘብ በፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ጉልህ ሚና ለመጫወት በጥምረት መስራት አንገብጋቢ መሆኑን በመረዳት ተጣምሮ በግንባር ለመስራት ተስማምተናል ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

ይህን ስምምነት የተፈራረሙት ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ ኢትዮጵያ ከረሃብ፣ ከበሽታና ከመሃይምነት የተላቀቀች ሆና፣ የሰብዓዊ መብቶች የተከበሩባት፣ በፍትሕና በእኩልነት ላይ የተመሰረተ አንድነትና ዴሞክራሲ የሰፈነባት እንድትሆን፣ ለብዙ ዓመታት የታገሉና ወደፊትም በእነዚህ እሴቶች ላይ በመመርኮዝ፣ ትግሉን ለማስቀጠል ጽኑ እምነት ያላቸው መሆኑን በመግለጫቸው ተናግረዋል፡፡

የመግባቢያው ሰነድ ከተፈረመ በኋላ፣ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን ለማዘጋጀት ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በመነጋገር፣ አስፈላጊውን እንቅስቃሴ ለማድረግ የሚሰሩ ከእያንዳንዱ ፓርቲ ሦስት ሦስት ኃላፊነት ያላቸው ተወካዮች ይኖሩታል፡፡ ኮሚቴው የሚያከናውነው የሥራ ውጤት በእያንዳንዱ አባል ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እየተገመገመ የሚያልፍና የሚጸድቅ ይሆናል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 16 የካቲት 23 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here