10 ከፍተኛ የነዳጅ ፍጆታ ያላቸው አገራት

0
916

ምንጭ፡- ወርልዶ ሜትር (2022)

ነዳጅ መሠረታዊ የኃይል ምንጭ በመሆን የምትክ ያለህ እየተባለ የሚደከምለት ነው። የኤሌክትሪክ መኪና፣ በፀሐይ ኃይል የሚሠሩ መሣሪያዎች ወዘተ ይህን ፍጆታ ለመቀነስ ነው እየታሰሱና እየተተገበሩ፣ ወደ ተግባር መውረዳቸውም ዜና ሆኖ እንደ ትልቅ ነገር እየተወራ ያለው።

ወርልዶ ሜትር የተባለ የቁጥር መረጃዎችን ይፋ የሚዲርግ ገጽ ላይ እንደምናየው፣ በዓለማችን ከፍተኛ የነዳጅ ፍጆታ ያላትና ከዓለምም የነዳጅ ሀብት ከፍተኛውን መጠን አገልግሎት ላይ የምታውለው አሜሪካ ናት። ከዛ ቀጥሎ በተወሰነ ልዩነት ቻይና ስትከተል፣ በከፍተኛ ልዩነት ዝቅ ብላ ሕንድ ትገኛለች።

በዚህ 214 አገራት በተዘረዘሩበት የወርልዶሜትር ዘገባ፣ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆና በዓለም ደግሞ 25ኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ግብጽ ናት። በመቀጠልን 29ኛ ደረጃ ላይ ደቡብ አፍሪካ ትገኛለች።
የነዳጅ ማደያ ሰልፍ ጉድ በሚባልባት ኢትዮጵያ፣ በዝርዝሩ 88ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን፣ ከዓለም ፍጆታ ላይ ድርሻዋ 0.076 በመቶ ብቻ ሆኖ ይገኛል።


ቅጽ 4 ቁጥር 184 ግንቦት 6 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here