ከ1500 በላይ ኢትዮጵያዊያን ከሳኡዲ አረቢያ እንዲመለሱ እየተሰራ ነው

0
791

በሳኡዲ አረቢያ ያለመኖሪያ ፍቃድ የሚኖሩና አንዲ ሺሕ 540 ኢትዮጵያዊያንን ለመመለስ እየሰራ እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ገለጸ።

የሚንስቴሩ ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት በይፋዊ የፌስ ቡክ ገፁ ካሰፈረው መረጃ ከሳኡዲ ወደ አገራቸው ለመመለስ የታሰበው አንድ ሺሕ 540 ዜጎችን እንደሆነ መረዳት ተችሏል።

ከሳኡዲ አረቢያ መንግሥትና ከዓለም ዐቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር የካቲት 20 ያለመኖሪያ ፈቃድ ይኖሩ የነበሩ 440 ኢትዮጵያዊያንን በራሳቸው ፈቃድ ወደ አገራቸው ስለመመለሱ የገለጸው የቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት የካቲት 19 በነበረው ውሎው 600 ኢትዮጵያዊያንን እንደመለሰም አስታውሷል። በቀጣይ ቀናት ቁጥራቸው 500 የሚደርሱ ዜጎች ከሳኡዲ አረቢያ እንደሚመለሱም አሳቀውቋል።

በዚህም ይመለሳሉ ከተባለው 1540 ኢትዮጵያዊያን መካከል 1040ዎቹ መመለሳቸውን መረጃው ያስረዳል።

ሳኡዲ አረቢያ ከዓመት በፊት ያለ መኖሪያ ፍቃድ በአገሯ የሚገኙ የሌላ አገር ዜጎች ግዛቷን ለቀው እንዲወጡ የ3 ወራት ማስጠንቀቂያ መስጠቷ እና ቀነ ገደቡ

መጠናቀቁን ተከትሎ በሳኡዲ ለመኖር ሕጋዊ አይደላችሁም የተባሉ የውጭ አገር ዜጎችን በኃይል ወደ ማስወጣት እርምጃ መሻገሯ ይታወሳል፡፡

በሳኡዲ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚገመቱ ኢትዮጵያዊያን በቤት ሰራተኝነትና ሌሎች የሥራ ዘርፎች ተሰማርተው እንደሚገኙ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 16 የካቲት 23 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here