10ቱ በብዛት ወደ ውጭ የተላኩ ምርቶች (ሐምሌ – መስከረም 2011)

0
490

ምንጭ፡-ብሔራዊ ባንክ፤ 2018

ከባለፉት ዓመታት አንፃር የ2011 በጀት ዓመት አዳዲስ ኹነቶች ያጋጠሙበት ወቅት ነበረ። ለአብነት ያህል፤ ወደ ወጭ የተላከው የጫት ምርት ከፍተኛ ጭማሪ በማሳየት ኹለተኛ በብዛት የተላከ ምርት ሆኖ ተመዝገቧል።

ለባለፉት ሦስት ዓመታት ጫት አብቃይ ቦታዎች የነበረው አለመረጋጋት በአንፃሩ መሻሻል ማሳየቱ ለምርቱ መጨመር እንደ ምክንያት ተጠቅሷል።
በሌላ በኩል ወደ ውጭ የተላከው የወርቅ ምርት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃፀር ከ45 ነጥብ 2 በመቶ በላይ ቅናሽ አሳይቷል።

በተመሳሳይ ወደ ወጭ የተላከው የቁም ከብት የ51 ነጥብ 4 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል። ከፍተኛ ገቢ በማስገኘት ቀዳሚ የሆነው የቡና የውጭ ንግድ በ 5 ነጥብ 2 በመቶ ቀንሷል።

ቅጽ 1 ቁጥር 16 የካቲት 23 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here