የኦሮሚያ መንግሥት አ/አ ኮንዶሚኒየም ማስተላለፏን ተቃወመ

0
1274

በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ መካከል ያለው የአስተዳደር የወሰን ጉዳይ አልባት እስከሚያገኝ የኦሮሚያ ክልልን ጥያቄ እያነሳባቸው ያሉ የክልሉን ወሰን አልፈው የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች በዕጣ ማስተላለፍ ትክክል እንዳልሆነ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ተቃውሞውን አሰማ።

በመሆኑም ይህ ውሳኔ ሥራ ላይ እንዳይውል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ጠንካራ አቋም መያዙን የክልሉ መንግሥት ካወጣው መግለጫ ለማወቅ ተችሏል። ይህ አቋም በቀዳሚነት የሕዝቡን ተጠቃሚነት በማስጠበቅ የመነጨ እንጂ የአገሪቱን ብሔር ብሔረሰቦች አብሮ የመኖር እሴት ከመጥላት የመነጨ አለመሆኑ ከግንዛቤ ሊገባ ይገባል ሲል ክልላዊ መንግሥቱ በመግለጫው አትቷል።

በጉዳዩ ላይ የአዲስ አበባን አቋም ለማወቅ አዲስ ማለዳ የከንቲባ ጽሕፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎችን በተደጋጋሚ ብትጠይቅም መረጃ ለመስጥ አልፈቀዱም፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 17 የካቲት 30 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here