የሕንዱ ኩባንያ የ44 ሰራተኞቹን ደመወዝ እስካሁን አልከፈለም ilfs

0
674

አይ ኤል ኤፍ ኤስ የተሰኘው የሕንድ መንገድ ተቋራጭ በኪሳራ ምክንያት የድርጅቱ ሠራተኞች የደመወዝ ይከፈለን ጥያቄ ባለመመለሱ አራት ሕንዳዊያን ከኅዳር 2011 ጀምሮ በቡሬ ካምፕ መታገታቸው ይታወሳል። ድርጅቱም የሰራተኛውን ደመወዝ ይከፈላል በሚል ባደረገው ድርድር አራቱን ሕንዳዊያን በየካቲት መጨረሻ ቢያስለቅቅም እስካሁን ለ44 ሰራተኞች ደመወዝ አለመክፈሉን የሕንዱ ቢዝነስ ላይን ዘግቧል።

እስካሁን ቁጥራቸው 44 የሚደርሱ የድርጅቱ ሠራተኞች ደመወዝ ሳይከፈላቸው በችግር ውስጥ እንደሚገኙ የተገለጸ ሰሆን፣ ከእነዚህ ውስጥም አንዱ ሰራተኛ እራሱን ለማጥፋት ሙከራ አድርጎ እንደነበር ቢዝነስ ላይን በድረ ገጹ አስነብቧል።

በድርጅቱ ካዝና ውስጥ ምንም ገንዘብ የሌለ በመሆኑ ክፍያውን ለመፈጸም ኩባንያው እንደሚቸገርም የመገናኛ አውታሩ የድርጅቱን ከፍተኛ ኃላፊ ዋቢ አድርጎ ባወጣው ዘገባ አስነብቧል።

ቅጽ 1 ቁጥር 17 የካቲት 30 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here